Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

Addisu Worku/Yemesqelu Feqer/Kebur Kebur

2006 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ብዙ ሃያላን ነበሩ

በአምላኬ ላይ የተኩራሩ

ቅዱሱን ሀይል የተገዳደሩ

ያ ዝናቸው አምድ ለብሶ

ታሪካቸው ተቀልብሶ

አለ ጌታ በላያቸው ነግሶ

ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር

ለዘለዓለም የምትኖር

አምላካችን እግዚአብሔር (፪x)

ሃብታም በሃብቱ ይኮራል

ሃያል በኃይሉ ይመካል

ስልጣን ያለው ጭቁኑን ይንቃል

ነገር ግን ቅኑ ፈራጅ ከላይ

ተቀምጧል ከዙፋን ላይ

ክንደ ብርቱ ጻድቁ ኤልሻዳይ

ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር

ለዘለዓለም የምትኖር

አምላካችን እግዚአብሔር (፪x)

የመከራ ወንዝ ሲሞላ

የጐበዝ ወኔ ሲላላ

ማነው ጽኑ ከአምላካችን ሌላ

የፈረሰ ሕይወት ጠጋኝ

ሁሉ ሲክድ ቀሪ ታማኝ

እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ታማኝ

ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር

ለዘለዓለም የምትኖር

አምላካችን እግዚአብሔር (፪x)

ለዛለው ምርኩዝ ደጋፊ

የደከመን አሳራፊ

ሁሉን ታጋሽ ፍፁም ልበ ሰፊ

የመሸበት አሳዳሪ

ለተጠቃ ተቆርቋሪ

እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ነዋሪ

ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር

ለዘለዓለም የምትኖር

አምላካችን እግዚአብሔር (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ