ምን ደላው ለእርሱ
Men Delaw Lersu
2006 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልደቱ በረት ሞቱ በመከራ እንጨት ላይ
ዕድሜውን ፈጅቶ በስቃይ
ለማልጠቅመው ለእኔ ጌታ እራሱን ጐዳ
ፍርድ ተሸክሞ ወደ ሞት ተነዳ
አዝማች · Chorus
ምን ደላው ለእርሱ ምን ደስ አሰኘው
የመስቀል ላይ ጣሩ እንደምን ማቀቀው
አዬ ፍቅር ሆኖ ሞተ እንደተገፋ
የእሾህ አክሊል ጭኖ አለ አንገቱ ደፋ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፍቅርን ለብሶ ርህራሄ አስገድዶት
የነፍሴ ለቅሶ ተሰምቶት
መጣ የእኔ ጌታ ሞተ ተጐሳቁሎ
የአባቱን ፍቃድ ፈጽሞታል ታግሎ
አዝማች · Chorus
ምን ደላው ለእርሱ ምን ደስ አሰኘው
የመስቀል ላይ ጣሩ እንደምን ማቀቀው
አዬ ፍቅር ሆኖ ሞተ እንደተገፋ
የእሾህ አክሊል ጭኖ አለ አንገቱ ደፋ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምን ዋልኩለት ለእዚህ ወዳጅ ከቶ
ለሞተው እኔን ተክቶ
አልተገራም ልቤ አልታረቀም ገና
መቼም ተስፋ አልቆርጥ ቀን ይመጣልና
አዝማች · Chorus
ምን ደላው ለእርሱ ምን ደስ አሰኘው
የመስቀል ላይ ጣሩ እንደምን ማቀቀው
አዬ ፍቅር ሆኖ ሞተ እንደተገፋ
የእሾህ አክሊል ጭኖ አለ አንገቱ ደፋ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ