Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምንሃለሁ

Amnehalehu

2006 · ትራክ 6 · 4:04 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለእምባዬ ዋጋ ያጣሁ

ጸሎቴን ያልሰማህ ሲመስለኝ

ጌታዬ ሆይ አምንሃለሁ

በችግሬ አንተን እንድትረዳኝ

አምንሃለሁ አምንሃለሁ

የተናገርከው እንደሚሆን

በክብር ከላይ ስትመጣ

ስለጣን ሁሉ በእጅህ እንዲሆን

ክንዴ ላልቶ ረዳት ሽቶ

ወደታችም ማቆልቆል ስጀምር

ረድተኸኛል በመንፈስህ

ጉዞዬንም በተስፋ እንድቀጥል

መድሃኒቴ መድሃኒቴ

ልጠለልህ መከራን እስክሸሽ

በአንተ ሕይወት እንድጸና

እንድቆም የዓለም ጊዜ እስኪመሽ

በእምነት ሳይህ ስትጣራ ደም እያዘነበ ከጐንህ

እያነባው እመጣለው ይሰማኛልና ስቃይህ

ተቀበለኝ የእኔ ጌታ በሌላ ልድን አልሞክርም

የሚያዝንልኝ የሚወደኝ እንደአንተ ያለ ከቶ አላገኝም

ከመስቀል በስተኋላ የሚኖረውን ታላቅ ፍዳ

ለመቀበል መርጫለሁ ከመጠበቅ የሞትን እዳ

ይሁንልኝ ይህ ፈቃድህ ጸሎቴም በፊትህ ትሰማ

ከአንተ ፍፁም እንደልለይ የሕይወት ጠዋት እስክትጠባ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ