Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እስቲ ና

Esti Na

2006 · ትራክ 5 · 6:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሳይሳሱ ፍቅሩን ወግተው ውርደት አለበሱት

ስለፈወሳት ብለው ባፈቀረ ጠሉት

የደሃ አዛኝ የሆንከው አንተ ነህ ኢየሱስ

ይገባ ነበረ ወይ ለእኔ ያፈጉት ነፍስ

የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ ኢየሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና (፪x)

አንተ ፍቅር ነህና ልትጠላኝ አቃተህ

ነፍሴን ከእሳት አወጣህ እራስህን ጐድተህ

የእኔ የሆነ ምን አለኝ እራሴም የአንተው ነኝ

ስለዚህ ጌታዬ ሆይ ደጋግመህ አድምጠኝ

የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ ኢየሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና (፪x)

ኑሮዬና ተግባሬ ለእኔ ባይጥመኝም

ጠላቴ የወጋኝ ቢያደናቅፈኝም

አንድ ጊዜ ቆርጬ ተከትዬሃለሁ

ድካም እንኳን ቢያጠቃኝ እከተልሃለሁ

የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ ኢየሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና (፪x)

ያ የምድር ጨለማ አይሎ እንዳይውጠኝ

መንፈስ ቅዱስ ጌታዬ ሳጠፋ ገስጸኝ

መንበርከክን ይወዳል ሥጋ ለዓለም ነገር

ጽናትህን እሻለሁ ከቶ እንዳልቀየር

የእግዚአብሔር በግ የሆንከው

ልቤን በፍቅርህ ያበስከው

ጓዴ ኢየሱስ እስቲ ና

የማዋይህ አለኝና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ