Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኢየሱስ

Eyesus

2006 · ትራክ 9 · 3:39 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኑሮ ያለ ጌታ ታክቶኝ ኀጢአቴ አስመርሮኝ

ወደ ኢየሱሴ ብመለስ የእርሱ ደግነት ማርኮኝ

በድል ጐዳና ብገባ ፍቅሩ ነፍሴን ብትፈታ

ጉልበቴን ለጠላት ላልሰጥ ቃል ገባሁኝ ለጌታ

በመከራና በጭንቀትም ሁሉ ጌታን አመልከዋለሁ

ኑሮ ያለእርሱ ጉዳት ነው ከእርሱ ጋር ግን ደስታ

የመልካም ሁሉ መሰረት ይመስገን የእኛ ጌታ

ስንጨነቅ የሚራራ ስንደክም ደጋፊያችን

በበረሃ ዓለም እያለን ስንጠማ እርካታችን

ዞሮ መግቢያችን ኢየሱስ ማረፊያችን አንተ ነህ

ብንከዳህ አያዋጣንም የድሃ ጐጇችን ነህ

ጌታ ጌታችን ጌታችን አስታውሰን (፪x)

ብለን ተጣርተን ሳናፍር እስካሁን ተጉዘናል

በነገር ሁሉ መጽናትን ከጌታ ተምረናል

የሚያሳፍር ስም አይደለም የሰጠኸን ጌታችን

ክርስቲያን ጀግንነት እንደው ይረዳልን ልባችን

ክፉውን ሁሉ ተቃውመን ከኀጢአት ጋራ ታግለን

ጉዟችን በድል ያከትማል የጌታን መስቀል ይዘን

ክብር ክብር ሃሌ ሉያ (፪x)

የነፍሳት ሁሉ ምሥጋና ዙፋንህን ይክበበው

በቸርነትህ ተገርሟል በልጅህ የዋጀኸው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ