Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታ ኢየሱስ ትዝ አልከኝ

Gieta Eyesus Tez Alkegn

2006 · ትራክ 8 · 4:49 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስደክም እያደገፈ ስወድቅ አንስቶ

ከእኔ ጋራ ተርቦ ስጠማ ተጠምቶ

በስስታ እያየኝ ልጄ በርታ ሚለኝ

ያ መልካሙ ጌታ ኢየሱስ በጣሙ ናፈቀኝ

ጌታ ኢየሱስ ትዝ አልከኝ ፤ ያደረክልኝ ውለታ

ከዳሁህ ተታልዬ ፤ ትቀበለኝ እንደው ወደ አንተ ልምጣ

ሌሎቹም ክርስቲያኖች ሄዱ በጣም ተጉ

በሕይወታቸው ግለው ወደ ድል ተጠጉ

ለዓለም አገልጋይ ሆኜ እኔ ግን ቀረኹኝ

ያችን ኢየሩሳሌምን ከሩቅ እያየሁኝ

ጌታ ኢየሱስ ትዝ አልከኝ ፤ ያደረክልኝ ውለታ

ከዳሁህ ተታልዬ ፤ ትቀበለኝ እንደው ወደ አንተ ልምጣ

ሰላምህ ከእኔ ሸሽቶ ጭንቀቴ እየገነነ

ያመንኩት ሁሉ ከዳኝ የያዝኩት ተነነ

ነፍሴ እንደተጐዳች ወዜም እንዳበረ

ጌታዬን ባገኘው ኖሮ እነግረው ነበረ

ብዬ ገና ስናገር ፤ ናልኝ ልጄ ሲል ሰማሁት

በእግሩ ስር ተደፍቼ ፤ ቅዱስ ጌታዬን ወየሁ ማረኝ አልኩት

ያለፈው ትምህርት ሆኖኝ የዓለም ጉስቁልና

ጉልበቴን ላላስገዛ ለዓለም እንደገና

ቃል ገባሁኝ በእርሱ ፊት ዳግም ላልለየው

የእኔን ጉስቁልና ለአየ መቀጣጫ ይሁነው

ለአንተ እገዛለሁኝ ፤ አንተ ነህ የነፍሴ ጌታ

ብቸገር ብጐሳቆል ፤ እድሌ አንተ ነህ ያለኸኝ አለኝታ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ