አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው
Adrashayie Mesqelu Ser New
ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በእንባና በጣር በጭንቅ በመከራ
በእሳት ውስጥ አልፎ ሕይወቴ ተገራ
ማዕበሉም ንፋሱም ሰራኝ ደህና አድርግ
ጠላት ለክፉ ሲል ሆነልኝ ለበጐ
ዛሬማ ወዳጄ ዐይኖቼ ተከፍተው አያለሁ አርቄ
የሕይወት ትርጉሙ በወጉ ገብቶኛል
እይዛለሁ አጥብቂ አድራሻዬን
አዝማች · Chorus
አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ መጽናናዬ መፈወሻዬ
መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
የብሶት የቋቱም ሲገነፍል ሞልቶ
እምነቴ ሲከዳኝ መታጠቂያው ላልቶ
የመለወጫዬ የጸሎቴ ቦታ
ድምጹን ሲያሰማኝ ሲያናግረኝ ጌታ
እጁ ስትዳስሰኝ ሸክሜን ሲያወርድልኝ ሁሉን እረሳለሁ
በሃዘን መጥቼ በእምባ ተንበርክኬ
በሳቅ እነሳለሁ አድራሻዬ
አዝማች · Chorus
አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ መጽናናዬ መፈወሻዬ
መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
ንፋሱ ባይነፍስ ባይታይ ደመና
እጠብቀዋለሁ ጌታ ብሏልና
ቃሉ አይታጠፍም ታማኝ ነው አምላኬ
ምስክር ቢያስፈልግ የትላንት ታሪኬ
የመጠበቂያዬን የጸሎቴን አምባ አልወጣም ለቅቄ
እስኪ መልስልኝ እማጸነዋለሁ
ከእግሩ ስር ወድቄ አድራሻዬ
አዝማች · Chorus
አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ መጽናናዬ መፈወሻዬ
መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
ያወቀ ይስታል የቆመም ይወድቃል
ብልህ ሰው ለነገው ስንቁን ይሰንቃል
የጭንቀቱ ጭጋግ የተስፋውን ጮራ
ሲሸፍነው ዋለ ወሬ ስናወራ
አሁን ይበቃናል ለወሬ በርትተን ለጸሎት መስነፉ
እንግባ ከጓዳ እዚያ ነው ሚገኘው
የበረከት ቁልፉ አድራሻዬ
አዝማች · Chorus
አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ (፪x)
መዳናዬ መጽናናዬ መፈወሻዬ
መስቀሉ ስር ነው አድራሻዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ