ታማኝ ነው በቃሉ
Tamagn New Beqalu
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወዳጄ አብርሃም
ፊቴ ተመላለስ
እኔን አይገደኝም
ኪዳኔን ለማደስ
እድሜ ሮጦ ሮጦ
ቢደርስ ጫፍ
ሰማይ ምድር ያልፋል
የኔ ቃል አያልፍም
አዝማች · Chorus
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ
ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የማያልፍ ምን አለ
እግዚአብሔር ከረዳ
የእምነት ምንጭ ይሆናል
ይሄ ምድረ በዳ
ያለው ይሄድና
ደግሞ ይመጣል ሌላ
ግዙፉ ተራራ
ይሆናል ደልዳላ
አዝማች · Chorus
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ
ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የመለኮት አዋጅ
ከመጣ ከሰማይ
ኢየሱስ ከአዘዘ
ይኬዳል ውኃ ላይ
ሙታን ይነሳሉ
እስራት ይፈታል
ቁራሹ ተባርኮ
ሺሆች ይበሉታል
አዝማች · Chorus
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ
ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌድዮንና ባርቅ
ዮፍታሄና ሳምሶን
ሳሙኤልና ዳዊት
ጳውሎስና ጴጥሮስ
የአንበሳን አፍ ዘጉ
እሳት አልበላቸው
ለታማኝነቱ ምስክሮች ናቸው
አዝማች · Chorus
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ
ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ምድያም በረሃ በፀሐይ ቃጠሎ
በቁጥቋጦ እሳት ራዕይ አቀብሎ
የፈርዖንን ክንድ በመቅሰፍት አድቅቆ
አሻግሮ የለም ወይ ህዝቡን አስለቅቆ
አዝማች · Chorus
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ
ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ጉድጓዱን ቆፍረህ ውኃ ስጣወጣ
ዞርበል የኔ ነው ባይ ምቀኛ ቢመጣ
እልፍ ብለህ ቆፍር ከሰው አትጣላ
ርሆቦት ይሆናል የኋላ የኋላ
አዝማች · Chorus
ታማኝ (፫x)
ታማኝ ነው እግዚአብሔር በቃሉ
ሰማይ ምድር እልል ይበሉ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ