ምንጩን ከፍቶ አሳረፈኝ
Menchun Kefto Asarefegn
ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የህይወት ጥማት አንገብግቦኝ ብዙ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፍለጋ ተንከራተትኩ
በበረሃ ስቅበዘበዝ ጌታ አገኘኝ
ምንጩን ከፍቶ አጠጥቶ አሳረፈኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔም እንደ አጋር ተሰድጃለሁ
በምድረ በዳ ተቅበዝብዣለሁ
ዐይኔን ቢከፍተው ሰጥቶኝ ማስተዋል
ለካስ ከጐኔ የውኃ ምንጭ ኖሯል
አዝማች · Chorus
የህይወት ጥማት አንገብግቦኝ ብዙ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፍለጋ ተንከራተትኩ
በበረሃ ስቅበዘበዝ ጌታ አገኘኝ
ምንጩን ከፍቶ አጠጥቶ አሳረፈኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በእኩለ ቀን በፀሐይ ንዳድ
መመላለሱ ከያዕቆብ ጉድጓድ
ከእንግዲህ በቃ እፎይ ብያለሁ
የሕይወትን ምንጭ ጌታን አገኘሁ
አዝማች · Chorus
የህይወት ጥማት አንገብግቦኝ ብዙ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፍለጋ ተንከራተትኩ
በበረሃ ስቅበዘበዝ ጌታ አገኘኝ
ምንጩን ከፍቶ አጠጥቶ አሳረፈኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ታሪክን ለዋጭ ተአምር ሰሪ
እስራት ፈቺ ቀንበር ሰባሪ
በምክር ታላቅ በስራ ብርቱ
ወደር የሌለው ለጌትነቱ
አዝማች · Chorus
የህይወት ጥማት አንገብግቦኝ ብዙ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፍለጋ ተንከራተትኩ
በበረሃ ስቅበዘበዝ ጌታ አገኘኝ
ምንጩን ከፍቶ አጠጥቶ አሳረፈኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ተቅበዝባዧ በግ በረት የሌላት
ነጣቂ ተኩላ የተከተላት
አዳኝ ታድኖ ታዳኙ ድኖ
ይኸው አየነው ስልጣን ተክኖ
አዝማች · Chorus
የህይወት ጥማት አንገብግቦኝ ብዙ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፍለጋ ተንከራተትኩ
በበረሃ ስቅበዘበዝ ጌታ አገኘኝ
ምንጩን ከፍቶ አጠጥቶ አሳረፈኝ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የሟርት የመተት የባዕድ አምልኮ
የጨለማው ሃይል ሰፈር ታውኮ
እስረኛው ወጣ ከግዞት አገር
የአምላኩ ዝና ለዓለም ይነገር
አዝማች · Chorus
የህይወት ጥማት አንገብግቦኝ ብዙ ዋተትኩ
የሚያረካኝን ፍለጋ ተንከራተትኩ
በበረሃ ስቅበዘበዝ ጌታ አገኘኝ
ምንጩን ከፍቶ አጠጥቶ አሳረፈኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ