Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰው ከንቱ

Sew Kentu

ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንገናኝ ነገ እንገናኝ ደህና

ዛሬን ለማደሩ መች አወቀውና

ሰው ከንቱ (፪x)

መንገዱን ሲያረዝም እቅዱን ሲያሰፋ

ዘንግቶት ይሆናል ታይቶ እንደሚጠፋ

ሰው ከንቱ (፪x)

ሰው ከንቱ (፮x)

ጌታ ብቻ ብርቱ (፪x)

ጀግና ወጥቶ ሲቀር ጐበዙ ሲቀጠፍ

ነገን እያሰቡ ከዛሬ አለማለፍ

ሰው ከንቱ (፪x)

ብዪ ጠጪ እያለ ነፍሱን ሲያዝናና

ሞት እንደ ደራሽ ወንዝ ድንገት ይመጣና

ሰው ከንቱ (፪x)

ሰው ከንቱ (፮x)

ጌታ ብቻ ብርቱ (፪x)

ይህ ለእኔ ያ ለእኔ እዚም እዚያም እኔ

ካለው ካገደመው ሲቅበዘበዝ ዓይኔ

ሰው ከንቱ (፪x)

የነገሌ የዘር ነኝ ሃብቴም እንዳፈር

ማንና ምን ይሆን አብሮኝ ሚቀበር

ሰው ከንቱ (፪x)

ሰው ከንቱ (፮x)

ጌታ ብቻ ብርቱ (፪x)

በውበት መመካት ዕውቀት አለኝ ማለት

ህልም ሆኖ ሊቀር ከአፈር የገቡ እለት

ሰው ከንቱ (፪x)

አስተዋይ ከዛሬ የነገን ይመርጣል

እግዚአብሔርን ማወቅ ከሁሉን ይበልጣል

ሰው ከንቱ (፪x)

ሰው ከንቱ (፮x)

ጌታ ብቻ ብርቱ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ