የታደለ ምስጉን ነው
Yetadele Mesgun New
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሉም ሲባል ይኖራሉ (አሁሁሁ) ጠፉ ሲባል ይበዛሉ (ኦሆሆሆ)
ሲዋለዱ ብዙ መንታ (አሃሃሃ) ሩጫቸውን ማን ሊገታ (አሃሃሃ)
አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም ይበረታሉ
እንደ ንስር ይበራሉ እጥፍ ድርብ ያፈራሉ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው
ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ
እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ
በዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ
የታደለ ምስጉን ነዉ
ቁጥር 2 · Verse 2
በሰው ብልሃት የተሰራ (አሃሃሃ) በሥጋ ደም የሚመራ (አሃሃሃ)
ሃስቡን ለፍልስፍና (አሃሃሃ) እምነታቸው መች ሆነና (አሃሃሃ)
ይናገሩ ያዳናቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት ናቸው
ዲያቢሎስም ያውቃቸዋል ጊዜ ስጡኝ ይላቸዋል
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው
ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ
እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ
በዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ
የታደለ ምስጉን ነዉ
ቁጥር 3 · Verse 3
እሳት አለ በውስጣቸው (እሄሄው) ማንም አይችል ሊያጠፋቸው (እሄሄው)
አይቻሉም ሲነኳቸው (እሄሄው) ተዋጊ ነው አምላካቸው (እሄሄው)
ሰባኪዎች በመገለጥ ለዲያቢሎስ እሳት ረመጥ
ዘማሪዎች በበገና ይቀባሉ ገና ገና
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው
ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ
እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ
በዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ
የታደለ ምስጉን ነዉ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰይፍ አይዙም በእጃቸው (እሄሄው) የመንፈስ ነው መሳሪያቸው (እሄሄው)
እዩት እስቲ ይህን ምርኮ (ኦሆሆሆ) መንገደኛ አይደለም እኮ (ኦሆሆሆ)
የክርስቶስ ስም ያዳነው የካህናት መንግሥት ነው
የዓለም ብርሃን የምድር ጨው እንደ ከዋክብት የተረጨው
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው
ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ
እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ
በዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ
የታደለ ምስጉን ነዉ
ቁጥር 5 · Verse 5
ሟርት አይሰራም በእስራኤል ላይ (አሃሃሃይ) አስማት የለም በያዕቆብ ላይ (ይሄሄሄይ)
አይቆጠርም ብዛቱ (ዑሁሁሁ) ድንበር የለው ለግዛቱ (ዑሁሁሁ)
እግዚአብሔር እፍ ያለበት የፈጠረው ለበረከት
መድሃኒት ነው መፈወሻ ወሰን የለው መጨረሻ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው
ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀዉ
እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለዉ
በዓለም ምድረ በዳ በድል የመራዉ
የታደለ ምስጉን ነዉ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ