አልባስጥሮስ
Albastros
2018 · ትራክ 4 · 5:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መንገዴን አደራ ብዬ ሰጠሁት ለመድኃኒቴ
ከሁሉ አስቀድሜ ከወዳጅ ዘመድ ከእናት ከአባቴ
ዛሬን አየሁኝ በደግነቱ በምሕረቱ
አቀዳጀልኝ ዓመታቶቸን በቸርነቱ
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነው ታማኝ ነው
እኔም በተራዬ ላክብረው
ታማኝ ነው ታማኝ ነው
እኔም በተራዬ ላክብረው
ዘመን ከመጣልኝ እኔም በተራዬ ላክብረው
ተራው ከደረሰኝ እኔም በተራዬ ላክብረው
አዳኜ ኢየሱስን እኔም በተራዬ ላክብረው
ክብር የሆነልኝ እኔም በተራዬ ላክብረው
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ትልቅ ነው ማንንም ዓይንቅም
ደካማን በመጣል እርሱ አይታወቅም
ሰው የረሳውን ያስባል የተጣለውን ያነሳል
ማን ወድቆ ቀረ ተጥሎ ደጅ ተጥሎ ደጅ
ማን ወድቆ ቀረ ተጥሎ ደጅ ተጥሎ ደጅ
ቁጥር 3 · Verse 3
መንገዴን አደራ ብዬ ሰጠሁት ለመድኃኒቴ
ከሁሉ አስቀድሜ ከወዳጅ ዘመድ ከእናት ከአባቴ
ዛሬን አየሁኝ በደግነቱ በምሕረቱ
አቀዳጀልኝ ዓመታቶቸን በቸርነቱ
አዝማች · Chorus
ታማኝ ነው ታማኝ ነው
እኔም በተራዬ ላክብረው
ታማኝ ነው ታማኝ ነው
እኔም በተራዬ ላክብረው
ዘመን ከመጣልኝ እኔም በተራዬ ላክብረው
ተራው ከደረሰኝ እኔም በተራዬ ላክብረው
አዳኜ ኢየሱስን እኔም በተራዬ ላክብረው
ክብር የሆነልኝ እኔም በተራዬ ላክብረው
ቁጥር 4 · Verse 4
ክረምት ሆነ በጋ አይቀያየርም
ቀን የጐደለለትን ጀርባውን አሰጥም
አቅም ለሌለው ወገን አለኝታ
ለደከመው ሰው ብርታት መከታ
እውነትም አባት የሁሉ ጌታ የሁሉ ጌታ
እውነትም አባት የሁሉ ጌታ የሁሉ ጌታ
ቁጥር 5 · Verse 5
ትዝ ሲለኝ ውለታው
ኢየሱስ ለእኔ ያረገው
አይሆንልኝ ዝም ማለት
ታሪኬ እኮ ነው ሰው የሆንኩበት
ቁጥር 6 · Verse 6
አልባስጥሮሴን ልስበረው
ውዴ ኢየሱስን ላክብረው
የእኔ ክብር የእኔ ደስታ
ሲከብርልኝ ነው ይህ ጌታ
አልባስጥሮሴን ልስበረው
ውዴ ኢየሱስን ላክብረው
የእኔ ክብር የእኔ ደስታ
ሲከብርልኝ ነው ይህ ጌታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ