አመልክሃለሁ
Amelkihalew
2018 · ትራክ 3 · 5:55 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምን እላለሁ እኔ ምን እላለሁኝ
ምን እላለሁኝ መነ እላለሁኝ
ስትረዳኝ እያየሁ ስታግዘኝ ስታግዘኝ ስታግዘኝ
የቱን ዘምሬ የቱን እተዋለሁ
ለኔ ያረክልኝ ከአይምሮ በላይ ነው
ለኔ ያረክልኝ ከአይምሮ በላይ ነው
መልካም ነህ ቢሉህ መልካምነትስ መቼ ይገልጽሃል
ፍቅር ነህ ቢሉህ የፍቅር ልኩ መቼ ይገልጽሃል
ኧረ ማን ልበልህ ማን ልበልህ
ቃል አጣሁልህ
ከተጣልኩበት አዘቅት መጥተህ
ከጠላቴ እጅ እኔን ተናጥቀህ
በደምህ ገዝተህ የአንተ ካረከኝ
እነዴት አልዘምር እንዴት አልቀኝ
ዛሬማ በላይ ሆኖአል ስፍራዬ
በአብ ቀኝ ሆኖአል መቀመጫዬ
ክብር ምሥጋና ለአንተ ይድረስህ
እድሜ ዘመኔን ልዘምርልህ
እንዴት ላመስግንህ
ኧረ እንዴት ላወድስህ
ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ
ሁለንተናዬን ለአንተ ሰጥቼ
በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ
ይኽው ላመልክህ መጥቻለሁ
አዝማች · Chorus
መልካም ነህ ቢሉህ መልካምነትስ መቼ ይገልጽሃል
ፍቅር ነህ ቢሉህ የፍቅር ልኩ መቼ ይገልጽሃል
ኧረ ማን ልበልህ ማን ልበልህ
ቃል አጣሁልህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሙት የነበርኩኝ በበደል ብዛት
ሕያው አረከኝ ነፍሴን ቀደስካት
ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠኽኝ
በትልቅ ፍቅርህ እንዲያው ወደድከኝ
ጽድቄ ነህና ቅድስናዬ
እንከን የሌለህ ንጽህናዬ
ብቃት የለኝም የምለው የእኔ
ቤዛ ባትሆነኝ አንተ መድኅኔ
እንዴት ላመስግንህ
ኧረ እንዴት ላወድስህ
ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ
ሁለንተናዬን ለአንተ ሰጥቼ
በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ
ይኽው ላመልክህ መጥቻለሁ
አዝማች · Chorus
አመልክሃልሁ
ዘላለሜ ኢየሱሴ የእንተ ነው
አመልክሃለው
የእኔ ጌታ ዘመኔን ውረሰው
ዘመኔ የአንተ ነው
ኑሮዬ የአንተ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ