ኤልሻዳይ
Elshaday
2018 · ትራክ 8 · 5:52 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መክፈት አይችልም ወይ ቁልፉ በእጁ አይደለም ወይ (፪×)
ኧረ ይችላል ኧረ ይችላል እንደ እኔ ያየ ይመሰክራል
ማክበር አይችልም ወይ ሥልጣን የእርሱ አይደለም ሆይ (፪×)
ቁጥር 1 · Verse 1
ኧረ ይችላል ኧረ ይችላል እንደ እኔ ያየ ይመሰክራል
ማገዝ አችልም ወይ ሥልጣን የእርሱ አይደለም ሆይ(፪×)
ኧረ ይችላል ኧረ ይችላል እንደ እኔ ያየ ይመሰክራል
ይችላል ያደርጋል ተወራርጃለሁ ነገሬን ሰርቶልኝ እኔማ አይቻለሁ
ይኸዉ ተገርሜ እዘምራለሁ ይኸዉ ተደንቄ እዘምራለሁ (፪×)
ቁጥር 2 · Verse 2
1በነቢያት መንፈስ እኔ እናገራለሁ በሞተዉ ነገር ላይ
ትንሳዔ አወራለሁ የደረቁ አጥንቶች የተበታተኑ
ትንቢቱ ሲመጣ ሰራዊቶች ሆኑ
ዛሬም ይሰራል ይሰራል ቃሉ ይፈጥራል ይፈጥራል የሌለን ነገር ያመጣል (፪×)
ዕድሜ ቀጥሎ ኑር አለኝና ዘማሬ ሰጥቶ ሞላኝ ምስጋና ዕልልታ ሆኗል
መታወቂያዬ ሞልቶ ይፈሳል ሐሴት ደስታዬ
ምድረበዳዉን ኤደን በረሐዉ ንገነት አደረገዉ አሀ ቀያየረና አሀ አደረገዉ
ከዓለቱ ላይ ምንጭን አፍልቆ አጠጣዉ ለተጠማዉ አሀ ተአምር ሰራና አሀ ለተጠማዉ
ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ ከሁኔታዎች በላይ
ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ ከኃያላኖች በላይ
ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ………………….
አዝማች · Chorus
መክፈት አይችልም ወይ ቁልፉ በእጁ አይደለም ወይ (፪×)
ኧረ ይችላል ኧረ ይችላል እንደ እኔ ያየ ይመሰክራል
ማክበር አይችልም ወይ ሥልጣን የእርሱ አይደለም ሆይ (፪×)
ቁጥር 3 · Verse 3
ኧረ ይችላል ኸረ ይችላል እንደ እኔ ያየ ይመሰክራል
ማገዝ አችልም ወይ ሥልጣን የእርሱ አይደለም ሆይ(፪×)
ኧረ ይችላል ኸረ ይችላል እንደ እኔ ያየ ይመሰክራል
ይችላል ያደርጋል ተወራርጃለሁ ነገሬን ሰርቶልኝ እኔማ አይቻለሁ
ይኸዉ ተገርሜ እዘምራለሁ ይኸዉ ተደንቄ እዘምራለሁ (፪×)
ቁጥር 4 · Verse 4
2 -አላሳልፍ ያለኝ የብረቱ መዘጊያ አዉቆ ተከፈተ
ሆነልኝ ማለፊያ እግ/ር መንገዴን ቀና ካደረገዉ
ከፍ ከፍ እንዳልል ከልካይ እረ ማነዉ
ሂድ ተከናወን ብሎኛል ዉጣና ዉረስ ብሎኛል አዝማቼ ከፊቴ ቀድሟል ፪×
ሕልም ብዬ የነገርኳቸዉ የማይፈፀም ቅዠት መስሏቸዉ
ያንን ሕልመኛ እንየዉ ሲሉ ጌታም ታማኝ ነዉ መጣ እንደ ቃሉ
ወደ ሹመት ስፍራ መፃተኛዉን ሰዉ አፈጠነዉ አሀ አሰቸኮለና አሀ አፈጠነዉ
ወገን በሌለበት በባእድ ምድር ላያ አነገሰዉ ሸላለመና አነገሰዉ
ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ ከሹማምንቶች በላይ
ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ ከመኳንንቶች በላይ
ኤልሻዳይ ኤልሻዳይ………………….
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ