Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

Teodros Tadesse/Wa/Adegedegalew

2018 · ትራክ 13 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ደሞ ልቀኝ ነዉ ዘመን መጣልኝ አሆ ዘመን መጣልኝ

ገብቼ ለማጠን ዕጣ ወጣልኝ አሆ ተራዉ ደረሰኝ

መታደል ነዉ መታደል ይሄን ጌታ ማገልገል

መታደል ነዉ መታደል ይሄን ጌታ ማገልገል

አደገድጋለዉ በፊቱ ልብሰ ተክኖዬን ለብሼ

የአዲስ ኪዳን ካህን ነኝና ገባዉ ላመልከዉ መቅረዜን ለኩሼ

ተደርጎልኛል ተደርጎልኛል ዝምታ በእኔ መች ያምርብኛል

ተፈቅዶልኛል ተፈቅዶልኛል የፈሰሰዉ ደም እለፍ ብሎኛል

እንደ አቤል መሥወእት ከተቀበለልኝ የእኔንም ዝማሬ

እርሱን ደስ ካለዉ ዘመኔ ይጠቅለል ዘምሬ ዘምሬ

መዝሙር አላቆምም እስትንፋሴ እስካለች በዚች ምድር ላይ

ሌላ ምን ስራ አለኝ የተፈጠርኩትስ ለዚማ አይደል ሆይ

አሆ ያርግልኝ አሆ አምልኮዬ አሆ ያለኝ ይኽዉ አሆ ይኽዉ ስጦታዬ

አሆ ያርግልኝ አሆ አምልኮዬ አሆ ያለኝ ይኽዉ አሆ ይኽዉ ዕልልታዬ

ይገባዋል እለዋለሁ በሙሉ ክብሩ ፊቱን እያየሁ

ይገባዋል እለዋለሁ በሞገሱ ፊቱን እያየሁ

ቃሉ ነግሮኛል ተከፍቷል ብሎኛል ቅዱስተ ቅዱሳን መግባት ሆኖልኛል

ቃሉ ነግሮኛል ተከፍቷል ብሎኛል ቅዱስተ ቅዱሳን መግባት ሆኖልኛል

ደሞ ልቀኝ ነዉ ዘመን መጣልኝ አሆ ዘመን መጣልኝ

ገብቼ ለማጠን ዕጣ ወጣልኝ አሆ ተራዉ ደረሰኝ

መታደል ነዉ መታደል ይሄን ጌታ ማገልገል

መታደል ነዉ መታደል ይሄን ጌታ ማገልገል

አደገድጋለዉ በፊቱ ልብሰ ተክኖዬን ለብሼ

የአዲስ ኪዳን ካህን ነኝና ገባዉ ላመልከዉ መቅረዜን ለኩሼ

ተደርጎልኛል ተደርጎልኛል ዝምታ በእኔ መች ያምርብኛል

ተፈቅዶልኛል ተፈቅዶልኛል የፈሰሰዉ ደም እለፍ ብሎኛል

ከላይ ከዓርያም በዙፋኑ ላለዉ በሱር ፀባኦቱ

ሲዘምሩ ሰማዉ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ዜማቸዉ ዉበቱ

ሽታዉ ያዉደኛል የአምልኮ መዓዛ ይሄ ህልዉና

ነፍስ አይቀርልኝም ወርዶ ሲሸፍ ነኝ የክብሩ ደመና

አሆ ያርግልኝ አሆ አምልኮዬ

አሆ ያለኝ ይኽዉ አሆ ይኽዉ ስጦታዬ

አሆ ያርግልኝ አሆ አምልኮዬ

አሆ ያለኝ ይኽዉ አሆ ይኽዉ ዕልልታዬ

ይገባዋል እለዋለሁ በሙሉ ክብሩ ፊቱን እያየሁ

ይገባዋል እለዋለሁ በሙሉ በሞገሱ ፊቱን እያየሁ

ቃሉ ነግሮኛል ተከፍቷል ብሎኛል ቅዱስተ ቅዱሳን መግባት ሆኖልኛል

ቃሉን ነግሮኛል ተከፍቷል ብሎኛል ቅዱስተ ቅዱሳን መግባት ሆኖልኛል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ