አንተ የምትተኛ
Ante Yemetetegna
ትራክ 2 · 3:39 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሰማይ ብርሃን ጨለማውን ገፍፎ
ሲዖል ድል ተነስቶ ሞትም ተሸንፎ
በኃጢያት ተወግተው ደክመው ለወደቁ
ጥሪው ያስተጋባል ሙታን እንዲነቁ
አዝማች · Chorus
አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል
በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል
ቁጥር 2 · Verse 2
ማየት በሌለበት መስማት በጠፋበት
ምሬትና ፀፀት ለቅሶ ከሞላበት
ምንድን ነው የጣለህ እንደምንስ መጣህ
ከሕያዋን ምድር ፈጥነህ ለምን ወጣህ
አዝማች · Chorus
አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል
በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል
ቁጥር 3 · Verse 3
ከእንቅልፍ የምትነሳበት ሰዓት ነው
ጊዜህን መርምረው ዘመኑን እወቀው
እንግዲያውስ ንቃ ተነስ ተመላለስ
አንተም ተመልሰህ የጠፉትን መልስ
አዝማች · Chorus
አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል
በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል
ቁጥር 4 · Verse 4
ድፍረትህን አትጣል ብድራት አለና
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተነስ እንደገና
የደከመው እጅህ የዛለው ጉልበትህ
ዳግም ተጠናክሮ ያፈራል ሕይወትህ
አዝማች · Chorus
አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል
በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል
ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ