Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የአደባባይ ሰው ሆነህ

Yeadebabay Sew Honeh

ትራክ 3 · 3:41 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የአደባባይ ሰው ሆነህ

በየማዕዘኑ ላይ ቆመህ

ሰውን አይተህ በሰው ታይተህ (፪x)

በስወር አይቶ በግልጥ የሚከፍልህን

በከፍታ ላይ የሚያስኬድህን

ረስተህ የለም ወይ አሳዳጊ ጌታህን

በስውር የሚቀመጡ

ጌታቸውን የሚያደምጡ

የሕይወትን ቃል የሚያመጡ (፪x)

ሰውን ለማነጽ ነቅተው የሚታጠቁ

ለበጐ ሥራ ሁሉ የሚበቁ

ምስጉኖች ናቸው መማለድን የሚያዉቁ

ከእግዚአብሔር የተላከ

እርሱ ነው የተባረከ

ቃሉን ብቻ እየሰበከ (፪x)

አንተንስ ማነው አስነስቶ የላከህ

በፍጻሜው ላይ ትጠየቃለህ

እንደ ሥራህም ያኔ ትከፈላለህ

ሥራህ ድካምህ ብዙ ነው

አንተነትህን ያጐላው

ጌታ እንዳይታይ የጋረደው (፪x)

እስኪ በእውነት መርምረው ሕይወትህን

መፀለይ ትተህ መራቆትህን

ኢየሱስን ጋርደህ አንተ መታየትህን

ስማው ኢየሱስ ይመክርሃል

"ተው ፣ እረፍ ፣ ፀልይ" ይልሃል

ከእግሮቹ ሥር ሥጋህን ጣል (፪x)

ያን ጊዜ ጌታ በሰገነት ላይ ወጥቶ

ለዓለም ይታያል ብርሃኑ በርቶ

ሕይወት ይበዛል የስንዴው ቅንጣት ሞቶ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ