አንተን ባየ ዓይኔ
Anten Baye Aynie
ትራክ 3 · 5:33 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሳይነጋ ለሊቱ ሳይቀድመኝ ጀንበር
መጥቻለው ፊትህ ለሊት ላከኝ ጉዳይ
አንተን ባየ አይኔ ይስሃቄን አይቼ ንቄዋለው
ሳላንገራግር ሳራን ሳላማክር እሰዋዋለው
አንተን ባየ አይኔ ይስሃቄን አይቼ ንቄዋለው
ሳላንገራግር ሳራን ሳላማክር እሰዋዋለው
አዝማች · Chorus
ይሁና የኔ ሳቅ ለእርሱ
ይሁና ደስታዬ ለእርሱ
ይበሉኝ ባዶ የቀረ
ይበሉኝ የተሞኘ
ቀሎብኝ አይደም ለብ ሚሆነኝ ለኔ
ጠብቄ ያገኘሁት ሚሳሳለት አይኔ
እሱን አየሁና ትምክቴን በሙሉ ንቄዋለው
ድጋሚ ሳላስብ ግራ ቀኝ ሳላይ ሰጠዋለው
ሞኝ ነህ ይበሉኝ ያለህን ይበሉኝ
መካሪ ያጣህ ይበሉኝ ተሳሳትክ ይበሉኝ
እርሱን ካከበረ ከተቀበለልኝ ምን እሻለው
ካለኝ ብቻ ሳይሆን ራሴንም ጨምሬ ሰጠዋለው
ይሁና የኔ ሳቅ ለእርሱ
ይሁና ደስታዬ ለእርሱ
ይበሉኝ ባዶ የቀረ
ይበሉኝ የተሞኘ
ቁጥር 2 · Verse 2
ካረካህ አንተን ደስ ካሰኘህ
ሰዊልኝ ያልከኝ ደስታዬን ቢሆን
አንድ ለሊት አይደር አንድ ቀን አይዋል
ሰዊልኝ ያልከኝ በኔ ቤት አያድር
ካረካህ አንተን ደስ ካሰኘህ
ሰዋልኝ ያልከኝ ደስታዬን ቢሆን
አንድ ለሊት አይደር አንድ ቀን አይዋል
ሰዋልኝ ያልከኝ በኔ ቤት አያድር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ