ትሁን ፈቃድህ
Tihun Feqadeh
ትራክ 1 · 5:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተን አሳብቤ/አስታክኬ ለጥቅሜ የፀለይኩት ፀሎቴ
ፊትህን ሳይሆን እጅህን እያየሁ የወሰድኩት መልሴ
ህይወት ይሆናል ወይ ፊትህ ያልበራበት ምን ቢገኝ
ፀሎቴ ይገራ ልመናዬ ይመር መንፈስህ ያስተምረኝ x2
አዝማች · Chorus
ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ x4
ቁጥር 2 · Verse 2
ስለ አባትነትህ ሳይሆን ስለ ክርክሬ ራርተህ
ደጅህን ስለጠናሁኝ እዬዬ ማለቴን አይተህ
ፀሎቴን እንዳትሰጠኝ ካልሆነ ያንተ ደስታ
እንደ ቃየል ጠብቀኝ ብዬ ከፊትህ እንዳልወጣ x2
አንተ የሌለህበትን ፊትህ ያልበራበትን
አትስጣት ለነፍሴ ካንተ ሚለየኝን
አንተ ሳትኖር በኔ ብትሰጠኝ ከነዓኔን
በምን እለያለሁ ከሌላዉ ህዝብ እኔ
አዝማች · Chorus
ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ x4
ቁጥር 3 · Verse 3
አትህዲ ስትለኝ ከቤቴ
ያዉልህ ብለህ ፀሎቴ
አሳልፈህ ለኔ አትስጠኝ
ደስ ያለህን ብቻ አድርግልኝ
አትህዲ ስትለኝ ከቤቴ
ያዉልህ ብለህ ለምኞቴ
ለፈቃዴ እኔን አትስጠኝ
ደስ ያለህን ብቻ አድርግልኝ
አዝማች · Chorus
ትሁን ፈቃድህ በኔ አይሁን እኔ ያልኩት ለኔ x4
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ