ከተባለ ለአንተ
Ketebale Lante
5:22 · አማርኛ
የዛሬ ቀን አይተህልኝ እጄን የያዝክ ከልጅነቴ
የት ይደርሳል ብለህ ያልናቅከኝ ስትደግፈኝ እዚህ አደረስከኝ
አባት ነህ የአባት ልኩ
ወዳጅ ነህ የወዳጅ ልኩ
አልተውከኝም እስካሁን እድሜ
ተሸክመኸኛል ጥላ ሆነህ አጥሬ
ከተባለ ላንተ ምስጋና ኧረ ብዙ ነው እኔ ቤት ና
ከተባለ ላንተ አምልኮ እንደ ዳዊት ነው ማመልክህ እኮ
ልክ እስከማይኖረኝ ገደብን እስካጣ
ሜልኮል እስክትታዘበኝ አምልኮዬ ዛሬም ይበዛል
ያ ባለዝና ያ ባለዘውድ አንተ ባትጨመርበት
ማን ይለው ነበር ንጉስ ዳዊት
ያ ባለዘውድ ያ ባለዝና ከሆነው በላይ ቢሆን
ቢያንስበት እንጂ መች ይበዛና
ከበዛልኝ ምህረት ከቸርነትህ
አንዳች ማይገባኝ ደካማ ነበርኩኝ
በእኔ ጉልበት ሳይሆን በራስህ ተማምነህ
እንዳለፈ ውሃ ስንቱን አስረሳኸኝ
ካረክልኝ ከሆንክልኝ ሚተካከል ቃል ባይገኝም
አምልኮዬ ዝማሬዬ ዙፋንህን ይክበብልኝ
ዝማሬዬ ይክበብልኝ እልልታዬ ይክበብልኝ
ዝማሬዬ ይክበብልኝ አድናቆቴ ይክበብልኝ
ለመመረጥ ለመታሰብ ያልታደለ በሰው ፊት
አዝማች · Chorus
ወዳጅ ሆንከው በቤቱ ገባህ በጠለት ፊት እራሱን ቀባህ
አባት ነህ የአባት ልኩ
ወዳጅ ነህ የወዳጅ ልኩ
አልተውከኝም እስካሁን እድሜ
ተሸክመኸኛል ጥላ ሆነህ አጥሬ
ከተባለ ላንተ ምስጋና ኧረ ብዙ ነው እኔ ቤት ና
ከተባለ ላንተ አምልኮ እንደ ዳዊት ነው ማመልክህ እኮ
ልክ እስከማይኖረኝ ገደብን እስካጣ
ሜልኮል እስክትታዘበኝ አምልኮዬ ዛሬም ይበዛል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ