እንደ ኢየሱስ
Ende Eyesus
ትራክ 2 · 6:50 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንተ ኖረህ በዚህች ምድር ላይ
ምሳሌ ሆንከኝ እሩቅ እንዳላይ
እታች ወርደህ እግር እንዳጠብክ
ለኔም ይቅለለኝ ወርዶ መታዘዝ
ይኸውና ወዳጄ ሰውነቴን
ይኸውና ወዳጄ እኔነቴን/ማንነቴን
ይኸውና ሰጠሁህ መንፈስ ቅዱስ
ቁጥር 2 · Verse 2
ይኸውና አድርገኝ እንደ ኢየሱስ [፪×]
ቁጥር 3 · Verse 3
1. የዋህ አድርገኝ በልቡ ትሁት
እጀ ጠባቡን ቢቀሙት ካባውን ሚሰጥ
ክፉውን በክፉ የማልመልስ
የሚጠሉትን ከነፍሱ የሚወድ
የዋህ አድርገኝ እንደ ኢየሱስ
እጀ ጠባቤን ቢቀሙኝ ካባዬን ምሰጥ
ክፉውን በክፉ የማልመልስ
የሚገፉኝንን ከነፍሴ የምወድ
አዝማች · Chorus
ይኸውና ወዳጄ ሰውነቴን
ይኸውና ወዳጄ ማንነቴን
ይኸውና ሰጠሁህ መንፈስ ቅዱስ
ቁጥር 4 · Verse 4
ይኸውና አድርገኝ እንደ ኢየሱስ
ቁጥር 5 · Verse 5
በዚህች ምድር ለአንድ ነገር እሮጣለሁ
የኢየሱስን ፍለጋውን እከተላለሁ
በዚህች ምድር ለአንድ ነገር እታገላለሁ
መምህሬን እንድመስለው እሻለሁ
በዚህች ምድር ለአንድ ነገር እሮጣለሁ
የኢየሱስን ፍለጋውን እከተላለሁ
በዚህች ምድር ለአንድ ነገር እሮጣለሁ
ኢየሱስን እንድመስለው እሻለሁ
ቁጥር 6 · Verse 6
2. ትጉህ አድርገኝ ጸሎት የማልታክት
ብርቱ አድርገኝ ኃጢአት የሚጸየፍ
ሚሰራ እስኪመስል ኢየሱስን
በሞቱ እንኳን በመሰልኩት የሚልን [፪×]
ቁጥር 7 · Verse 7
ይህን መንገድ ይህን ሩጫ እሮጠዋለሁ
የኢየሱስን ፍለጋውን እከተላለሁ
ያግዘኛል ይረዳኛል መንፈስ ቅዱስ
ይሰራኛል እስክመስል እንደ ኢየሱስ
አዝማች · Chorus
ይኸውና ወዳጄ ሰውነቴን
ይኸውና ወዳጄ ማንነቴን
ይኸውና ሰጠሁህ መንፈስ ቅዱስ
ቁጥር 8 · Verse 8
ይኸውና አድርገኝ እንደ ኢየሱስ [፪×]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ