በመንፈስህ ክብር
Bemenfesih Kibir
ትራክ 1 · 5:05 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በመንፈስህ ክብር ነክረህ አረስርሰኸኝ
ምንም ነገር እንዳይጎል አርገኸኝ
ደስታዬ ፍፁም ነው እንከን የሌለው
አንተን ብቻ ብዬኮ ቀረው
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ የሁሉ ወዳጅ ነህ
የሁሉ ወዳጅ ነህ የሁሉ ወዳጅ ነህ
ኢየሱስ የሁሉ ወዳጅ ነህ
የሁሉ ወዳጅ ነህ የኔኮ ወዳጅ ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ትልቅ ቢሆን ትንሽ ደሃ ባለጠጋ
ፍቅርን ያገኛል ወደ አንተ ሲጠጋ (2x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የማይጠፋ እርስት እንከን የሌለው
ህያው ተስፋ አለኝ እሱም ጌታ ነው
ያስታውቅብኛል እንደ ተጋባብኝ
ያንተ መንፈስ እንደ ረበበብኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
በጨለማው አለም ሀዘን በሞላበት
በኔ ቤት ግን መዝሙር ፈለቀበት
አዝማች · Chorus
ከሁሉ በላይ ነው ለኔ
ከሁሉ በላይ (2x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የማይጠፋ እርስት እንከን የሌለው
ህያው ተስፋ አለኝ እሱም ጌታ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ