ብርሃን ነው ኢየሱስ
Berhan New Eyesus
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ብርሃን ነው ኢየሱስ ብርሃን ነው
ብርሃን ነው ኢየሱስ ብርሃን ነው
ጨለማን ያበራል ኢየሱስ ብርሃን ነው
በጨለማ ላለ ብርሃን ነው
ለተጨነቀ ሕዝብ መጽናናት ነው
ከሃጥያት የሚያድን ኢየሱስ ነው
እውነትና መንገድ ሕይወትም ነው
ለተጠማ የሕይወት ውኃ ይሰጣል
በእርሱ የሚታመን መች ይራባል
ዘላለም ከእርሱ ጋራ ይኖራል
ባባቱ ቤት መሰማሪያ ያገኛል
በእርሱ የሚያምኑ ይድናሉ
ከሃጥያት በደሙ ይነጻሉ
የዘለዓለም ሕይወት ይወርሳሉ
ከእርሱ ጋራ አብረው ይከብራሉ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ቅርብ ነው ይገኛል
የሚፈልገው ልብ ደስ ይሰኛል
ሸክምን ያራግፋል እረፍት ያሰጣል
አእምሮና ልብን ያስርፋል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ