ደስ ይለኛል በጌታዬ
Des Yelegnal Begietayie
ትራክ 8 · 6:54 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ይለኛል በጌታዬ
ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እወጣለሁ እገባለሁ እሰማራለሁ
የኢየሱስን ሰላም በሕይወቴ አያለሁ
በተከበበች ከተማ ምህረቱ ከቦኛል
በጌታ ደስ ይለኛል ሰላም ሆኖልኛል
አዝማች · Chorus
ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ይለኛል በጌታዬ
ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ማህበሉ ቢነሳም እንኳን ወጀቡም ቢበዛ
ነፍሴ እረፍት አላት በኢየሱስ ተይዛ
በለስ ፍሬ ባታፈራ የወይራ ስራም ቢጐል
እኔ ግን በአምላኬ በጌታ ደስ ይለኛል
አዝማች · Chorus
ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ይለኛል በጌታዬ
ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የልቤ ጥያቄ ሞልቶ ሁሉ ቢሆንልኝ
ለእኔስ እንደ ኢየሱስ አንድም አይሆንልኝ
የተሰወረውን ነገር የውስጥን ይረዳል
በእርሱ ደስ ይለኛል ከሁሉም ይበልጣል
አዝማች · Chorus
ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ይለኛል በጌታዬ
ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከታሰርኩበትም ፈቶ ነጻ አድርጐኛል
ውዴ በእኔ ላይ ከብሯል ከፍ ብላል
ኃጢአቴን አስወግዶልኝ ፅድቄ እርሱ ሆናል
በፊቱ ዘላለሁ በጌታ ደስ ይለኛል
አዝማች · Chorus
ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ይለኛል በጌታዬ
ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው ነፍሴን መልሷታል
በፅድቅም መንገድ ወደ እውነት መርቷታል
በጌታዬ በኢየሱስ በእርሱ እመካለሁ
በእርሱ ደስ ይለኛል ለእርሱ እገዛላሁ
አዝማች · Chorus
ደስ ይለኛል በኢየሱሴ/በአምላኬ
ደስ ይለኛል በጌታዬ
ሰላም ጤና ሆኗል ለኑሮዬ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ