Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማዳኑን አይቻለሁ

Madanun Ayechalehu

ትራክ 1 · 6:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከክፉው ካስፈሪው ኢየሱስ ታድጐኛል

ከጨለማ አውጥቶ ብርሃን ሆኖልኛል

በጠላቴም ፊት ዘይት ቀብቶኛል

ከሳሼን ጥሎልኝ እኔን አክብሮኛል

ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው

ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (፪x)

ሆኖልኛልና ከሰማይ

በባዕድ አገር ወገን አባት ሆኖልኛል

በአለቆችም ፊት ሞገስ ሆንልኛል

ወንዙን ማዕበሉን እርሱ አሳልፎኛል

በዚህ ክፉ ዘመን ጥላ ሆንልኛል

ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው

ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (፪x)

ሆኖልኛልና ከሰማይ

ሥሙ እንደሚፈስ ዘይት ሆኖልኛል

ልቤን በደስታ አፌን በሳቅ ሞልቷል

ሕጉ ለእግሬ መብራት ብርሃን ሆኖልኛል

እንዳልሰናከል ኢየሱስ ጠብቆኛል

ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው

ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (፪x)

ሆኖልኛልና ከሰማይ

ምህረት ቸርነቱ ፍቅሩ እኔን ከቦኛል

የማዳኑ ሥራ እጅግ በዝቶልኛል

ስተኛ ቀስቅሶኝ ስዝል ደግፎኛል

አለቱ ኢየሱስ በእጁ ይዞኛል

ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው

ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (፪x)

ሆኖልኛልና ከሰማይ

ለውለታው ሁሉ ምን እመልሳለሁ

ባወራው ባወራው አያልቅም ብዙ ነው

በሕይወት ዘመኔ ለእርሱ ዘምራለሁ

ተመስገን እያልኩኝ እቀኝለታለሁ

ማዳኑን ማዳኑን አይቻለሁ (፪x)

ጌታ ኢየሱስ ለእኔ አዳኜ ነው

ጥበቃው ጥበቃው በላዬ ላይ (፪x)

ሆኖልኛልና ከሰማይ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ