ከአንተ ልማር ኢየሱስ
Kante Lemar Eyesus
ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፍቅርን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
ምህረትን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
ይቅርታን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
የነፍሴ ንጉሥ የሕይወቴ ንጉሥ
የማይለወጥ የአንተ ፍቅር
የማትሰለች ሁልጊዜ ምትምር
ይቅርታህ ብዙ ከአይምሮ በላይ
ጌታ እንተን አየሁ በምድር በሰማይ
አዝማች · Chorus
ትዕግሥትን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
ቸርነት ከአንተ ልማር ኢየሱስ
ማስተዋል ከአንተ ልማር ኢየሱስ
የነፍሴ ንጉሥ የሕይወቴ ንጉሥ
ቁጥር 2 · Verse 2
አየሁኝ ጌታ ስትታገሰኝ
በቸርነትህ ስትለግሰኝ
ታስደንቃለህ ማስተዋል አለህ
ሚመስልህ የለም ኢየሱስ ልዩ ነህ
እውነትን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
ዕውቀትን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
ጥበብን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
የነፍሴ ንጉሥ የሕይወቴ ንጉሥ
አዝማች · Chorus
አንተ እውነት ነህ እውነተኛ ነህ
ሁሉን ፈጥረሃል ሁሉን ታውቃለህ
ጥበበኛ ነህ የሁሉ ጌታ
በምንም ነገር የማትረታ
ቁጥር 3 · Verse 3
የዋህነት ከአንተ ለማር ኢየሱስ
ትህትናን ከአንተ ልማር ኢየሱስ
መታዘዝ ከአንተ ልማር ኢየሱስ
የነፍሴ ንጉሥ የሕይወቴ ንጉሥ
አትጨክንም አንተ የዋህ ነህ
ዝቅ ማለትን ታውቅበታለህ
እስከሞት ድረስ አንተ ታዘዝህ
ኢየሱስ ሙሉ ነህ ትማርካለህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ