ክበር በሉት ኢየሱስን
Keber Belut Eyesusen
ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለናዝሬት ኢየሱስ እንደበግ ለታረደው
በደሙ ለእግዚአብሔር ሰዎችን ለዋጀው
ለአምላክ መንግሥትና ካህናት ላደረገው
በረከትና ክብር ምሥጋና ይድረሰው
አዝማች · Chorus
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት
ቁጥር 2 · Verse 2
ያለና የነበር የሚመጣው ሁሉን የሚገዛው ኢየሱስ ነው
አእላፋት መላእክት ያከብሩታል ተመስገን እያሉ ይሰግዱለታል
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት
ቁጥር 3 · Verse 3
ዛሬ ነው የደስታ የምሥጋናችን ቀን
መርገምን አርቆዋል ሰርታል ስራችንን
በፍፁም ፈቃዱ እንዲሁ አድኖናል
ስገድትም ምሥጋናም ለእርሱ ያንስበታል
አዝማች · Chorus
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት
ቁጥር 4 · Verse 4
አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያው የሁሉ ፍጻሜ መጨረሻው
የሚመጣው ንጉሥ ኢየሱስ ነው የዓለምን ሃጥያት ያስወገደው
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት
ቁጥር 5 · Verse 5
ባባቱ ቀኝ ላለው ለጌታ ለኢየሱስ
አምልኮ ዝማሬ ከልባችን ይፍሰስ
በክብር ታጅቦ በደመና ይመጣል
ያለም ፍጥረት ሁሉ ለክብሩ ይሰግዳል
አዝማች · Chorus
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት
ቁጥር 6 · Verse 6
በዙፋኑ ላለው ክብር እንስጠው ይገባዋል ስግደት እናክብረው
በምሥጋና ዜማ በዕልልታ በፊቱ እንዘምር በደስታ
አዝማች · Chorus
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት ኢየሱስን
ክበር በሉት አሜን ክበር በሉት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ