ኢየሱስ ፍቅር ነው
Eyesus Feqer New
ትራክ 2 · 6:07 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀማኛ ረብሸኛ ሌባ ተንኮለኛ
ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ እብሪተኛ ኃይለኛ
የፍቅር አባት ጋር ኢኢየሱስ ጋር ሲደርስ
ልቡ ይማረካል ይረታል በኢየሱስ
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
ሌባውን ታማኝ ያደርጋል
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
ረብሸኛን ሰላማዊ ያደርጋል
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል
በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል
ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል
ቁጥር 2 · Verse 2
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል
ብዙ ተመሬያለሁ የሚለኝ ሁሉን ቻይ
ዓለም ምን እንደሆን እኔ አውቃለሁኝ ባይ
የጥበብን መሰረት ጌታን ያገኝና
አምላኩን ይፈራል ዕውቀቱን ይረዳና
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
ትዕቢተኛን ትሁት ያደርጋል (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል
በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል
ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል
ቁጥር 3 · Verse 3
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ይማርካል
ተስፋ የቆረጠው በሰው የተናቀው
ታናሽ የተባለው ዕውቀትም የሌለው
የዕውቀትን ሚስጥር ኢየሱስን አግኝቶ
ሩቁን ማየት ችላል ማስተዋል ተሞልቶ
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
የተናቀውን ከፍ ያደርጋል
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
የተናቀውን ያስከብራል
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል
በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል
ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል
ቁጥር 4 · Verse 4
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል
የጐደለኝ የለም ሰላማዊ ሰው ነኝ
ተኛለሁ እረፍት አለኝ ደህና አለኝ ደስታ አለኝ
ሲል የኖረው ሀብታም ሲያደርግ እራሱን ደግ
ተረዳው በኢየሱስ መሆኑን የጠፋ በግ
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
ወደ ቤትም ያስገባል (፪x)
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል
በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል
ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል
ቁጥር 5 · Verse 5
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል
ሸባው በአልጋ ወድቆ በበሽታ ማቆ
ቆሞ መሄድ ችሏል ኢየሱስን አውቆ
የሞተው ተንስቷል የእውሩም ዓይን በርቷል
እርሱ ሁሉን ይችላል ታሪክ ይለውጣል
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
ሽባውንም ያራምዳል
ኢየሱስ ታሪክ ይለውጣል
የሞተውን ያስነሳል
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ያሸንፋል
በር ለከፈተለት ሁሉንም ይረታል
ኢየሱስ ያድሳል ታሪክ ይለውጣል
ቁጥር 6 · Verse 6
ኢየሱስ ፍቅር ነው ሁሉን ድል ያደርጋል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ