Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በየት ሃገር ነው እግዚአብሔር

Beyet Hager New Egziabhier

2013 · ትራክ 2 · 4:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በየት ሃገር ነው እግዚአብሔር

ሰው ጥሎ የሚያወቀው እግዚአብሔር (፬x)

እግዚአብሔር አይጥልሽም

እግዚአብሔር አይተውሽም

እግዚአብሔር አይረሳሽም (፪x)

እግዚአብሔር አይጥልህም

እግዚአብሔር አይተውህም

እግዚአብሔር አይረሳህም (፪x)

ዝም በሉ ዝም በሉ

በኩራት አትናገሩ (፫x)

እግዚአብሔር አዋቂ ነው

ስራውን ሚመዝን ነው (፫x)

የእኔ አምላክ አዋቂ ነው

ስራውን ሚመዝን ነው (፫x)

እግዚአብሔር አይጥለንም

እግዚአብሔር አይተወንም

እግዚአብሔር አይረሳንም (፪x)

እግዚአብሔር አይጥለንም

እግዚአብሔር አይተወንም

እግዚአብሔር አይረሳንም (፪x)

ሁሉም በየጓዳው ችግሩን እያየ

አንተን ለማመስገን እንደምን ዘገየ (፪x)

ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ

ሠማያትም ዘምሩ ኮረብቶች አጨብጭቡ

ተራሮች እልል በሉ

እግዚአብሔር ችግረኛውን አስቧል የተጐዳውን (፪x)

ዝም በሉ ዝም በሉ

በኩራት አትናገሩ (፫x)

እግዚአብሔር አዋቂ ነው

ስራውን ሚመዝን ነው (፫x)

የእኔ አምላክ አዋቂ ነው

ሥራውን ሚመዝን ነው (፫x)

ሥራውን ሚመዝን ነው (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ