ቅዱስ ቅዱስ
Qedus Qedus
2013 · ትራክ 9 · 8:14 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ያለና የነበረ የሚመጣ
ሁሉን የሚገዛ (፪x)
አዝማች · Chorus
እያሉ ቀንና ሌሊት አይርፉም (፬x)
የሠማይ ሰራዊት ያገለግሉሃል
በቀን በሌሊቱ ቅዱስ ነህ ይሉሃል (፪x)
እኔም በአቅሜ ከፍ አደርግሃለሁ
ሰው ላረከኝ ጌታ ምሥጋናን እሰዋለሁ (፪x)
እያሉ ቀንና ሌሊት አይርፉም (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መሆን እወዳለሁ ሁልጊዜ በፊትህ
ተመስገን እንድልህ እንዳገለግልህ (፪x)
መሆን እወዳለሁ ሁልጊዜ በፊትህ
ተባረክ እንድልህ እንዳገለግልህ (፪x)
መሆን እወዳለሁ ሁልጊዜ በፊትህ
ከፍ በል እንድልህ እንዳገለግልህ (፬x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ሃሌ (፬x)
አቤቱ አምላኬ ተወደስ
በልጆችህ ተቀደስ
ምሥጋናችን ለእአምላካችን
ያማረ ነው የሁላችን
ክብር ክብር ክብር ሃሌሉያ
ክብር ሃሌሉያ ክብር ሃሌሉያ
ሞገስ ሞገስ የሌለህ እኩያ
የሌለህ እኩያ የሌለህ እኩያ (፪x)
ሃሌሉያ (፫x) (ሃሌሉያ)
ሃሌሉያ (፪x) ሃሌሉያ
ሃሌሉያ (፫x) ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ሃሌ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በፍቅርህ ዘይት ነፍሴን አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ጌታዬ
በምህረትህ ዘይት ነፍሴን አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ጌታዬ
ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው
ደናግሎች አይተው ወደዱህ (፭x)
እኛም አየንህ ጌታ ወደድንህ
መልካም የመዓዛ ሽታ አንተ አለህ
እኔም አይቼ ይህን ውዴ ወደድኩህ
መልካም የመዓዛ ሽታ አንተ አለህ (፫x)
በፍቅርህ ዘይት ነፍሴን አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ጌታዬ
በምህረትህ ዘይት ነፍሴን አረስርሰሃል (፪x)
ተባረክልኝ ጌታዬ
አዝማች · Chorus
በማለዳ ምሥጋና በሌሊትም ዝማሬ
ሁኔታ አለወጥህ አንተ ነህ እስከዛሬ
በማለዳ ምሥጋና በሌሊትም ዝማሬ
ነገሮች አለወጡህ አንተ ነህ እስከዛሬ
አንተ ብቻ ነህ (፬x)
አንተ ብቻ ነህ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ስደክም ጉልበቴ ስበረታ ክብሬ
አንተ አልተለወጥክም ኢሄው እስከዛሬ
ቀናቶች ሲያልፉ አመታት ሲሆኑ
የነገሥታት ንጉሥ አለ በዙፋኑ
በማለዳ ምሥጋና በሌሊትም ዝማሬ
ሁኔታ አለወጥህ አንተ ነህ እስከዛሬ
በማለዳ ምሥጋና በሌሊትም ዝማሬ
ነገሮች አለወጡህ አንተ ነህ እስከዛሬ
አንተ ነህ እስከዛሬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ