ነፍሴን የሚያረካ
Nefsien Yemiyareka
2013 · ትራክ 1 · 7:05 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሌላ ነገር አይደለም ነፍሴን የሚያረካት
አምላክ ሆይ አንተ ናና በመገኘትህ አርካት
ሌላ ነገር አይደለም ነፍሴን የሚያረካት
አምላክ ሆይ አንተ ናና በመገኘትህ አርካት (፭x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አንዳንዶች ገንዘብ ይላሉ
አንዳንዶች ዝና ይላሉ
አንዳንዶች ዘመድ ይላሉ
አንዳንዶች ዕውቀት ይላሉ
እኔ ግን እርግጠኛ ነኝ
አንተው ነህ የምትበልጠው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ነህ
ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ አንተ ብቻ ነህ
ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ
ነፍሴ ወደደችህ ወዴት ትገኛለህ
ስፍራውን አሳየኝ የት ታሰማራለህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ብርና ወርቅ አያጓጓኝም
ልቤን አይነካኝም ዓይኔን አይስበኝም
የሚያጓጓኝ የእግዚአብሔር መንግሥት ነው
ርሃቤ ጥማቴ ጽድቁ ነው ጽድቁ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንተን ነው ነፍሴ የተጠማችው
አንተን ነው ነፍሴ የተመኘችው
የአንተን ስጦታ መፈለግ ትታለች
አንተን እራህን ትፈልጋለች
የአንተን በረከት መፈለግ ትታለች
አንተን ራስህን ትፈልግሃለች
ቁጥር 5 · Verse 5
ምን አዲስ ነገር አለ
ከዚህ ፀሐይ በታች
የእግዚአብሔር ልጅ ነው እንጂ
ለሰዎች የሚበጅ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ጌታ ኢየሱስ ነው እንጂ ለሰዎች የሚበጅ
ነፍሴ ወደደችህ ወዴት ትገኛለህ
ስፍራውን አሳየኝ የት ታሰማራለህ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
መዝገቤ እኮ አንተ ጋር ነው
መዝገቤ በሰማይ
መዝገቤ በአለበት
ልቤስ በዚያ አይደል ወይ (፫x)
ቁጥር 8 · Verse 8
ነፍሴ ወደደችህ ወዴት ትገኛለህ
ስፍራውን አሳየኝ የት ታሰማራለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ነህ
ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ አንተ ብቻ ነህ
ለሰዎች ሁሉ መፍትሄ ያለህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ