እግዚአብሔር አለልኝ
Egziabhier Alelgn
2013 · ትራክ 7 · 6:50 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር አለልኝ በቃ
እርሱ ይበቃኛል በቃ (፪x)
እግዚአብሔርን ሚበልጥ ሌላ ሌላ ሌላ አለ ወይ
ከእኔ አምላክ የሚሻል ሌላ ሌላ ሌላ አለ ወይ (፪x)
ሌላ ሌላ አለ ወይ (፬x)
ሌላ ሌላ አለ ወይ (፬x)
አዝማች · Chorus
አለልኝ ጌታ አለልኝ (፬x)
ጌታ አለልኝ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የልቤ ፍሰሃ ነህ ፍሰሃ ነህ ፍሰሃ
የነፍሴ ደስታ ነህ ደስታ ደስታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አለኝ አንድ ተስፋ ከቶ የማይጠፋ
ኢየሱስ ይባላል ነፍሴን ይመልሳል (፪x)
አለኝ አንድ ተስፋ ከንቱ የማይጠፋ
ኢየሱስ ይባላል ነፍሴን ይመልሳል (፪x)
ነፍሴን ይመልሳል (፬x)
አዝማች · Chorus
አለልኝ ጌታ አለልኝ (፬x)
ጌታ አለልኝ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ልዑል ሆይ ከልዑሎችም በላይ አንተ ልዑል ነህ
መተከያም መለኪያ የለውም ለልዑልናህ
ለልዑልናህ (፫x)
ለልዑልናህ (፫x)
ቁጥር 5 · Verse 5
በዙፋን ላይ ላለው ክብር ክብር ይሁንለት ይሁንለት
በማደሪያው ላይ ላለው ክብር ክብር ይሁንለት ይሁንለት
ይሁንለት (፬x)
ታናናሾች ታላላቆች ሁሉ ቅዱሳኑም የምትፈሩት
አምላካችንን አክብሩት (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
አምጡ ምሥጋናውን አምጡ
አምጡ ክብሩን አምጡ
አምጡ ክብሩን አምጡ
እስኪ አምጡ ምሥጋናውን አምጡ
አምጡ ክብሩን አምጡ
አምጡ ክብሩን አምጡ
ምሥጋናውን አምጡ ክብሩን አምጡ
ምሥጋናውን አምጡ ክብሩን አምጡ
ቁጥር 7 · Verse 7
ጌታን ነዉ የታወቀ በዓለም ዝናው የገነነ
ፍጥረት ሁሉ የሚሰግድለት ምላስ ሁሉ የሚያወራለት
ለዚህ ለእግዚአብሔር እሰግዳለሁ (፫x)
ለዚህ ለእግዚአብሔር እኖራለሁ (፫x)
ለዚህ ለእግዚአብሔር እግዛለሁ (፫x)
መጸለይ አለልኝ በቃ
እጸልያለሁኝ በቃ
ለእግዚአብሔር ነገርኩት በቃ
ለእግዚአብሔር ሰጠሁት በቃ
ከጸሎት ሚበልጥ ሌላ ሌላ ሌላ አለ ወይ
ከጸሎት የሚሻል ሌላ ሌላ ሌላ አለ ወይ (፪x)
ሌላ ሌላ አለ ወይ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ