ትልቅ ነህ
Teleq Neh
2013 · ትራክ 8 · 9:30 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ትልቅ ነህ የእኔ አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ (፬x)
ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (፫x)
ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (፫x)
እግዚአብሔር ትልቅ ነው አምላኬ ትልቅ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ትልቅነትህን ያላየ ማነው (፫x)
ትልቅነትህን ያልሰማ ማነው (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔስ አይቻለሁ ትልቅነትህን
ከሁኔታ በላይ አንተ መብለጥህን
እኔ እንኳን አይቻለሁ ትልቅነትህን
ከነገሮች በላይ አንተ መብለጥህን
እኔ አይቻለሁ ትልቅነትህን
ከሁኔታዎች አንተ መብለጥህን
አንተ እኮ እጅግ ትልቅ ነህ (፪x)
አምላኬ እጅግ ትልቅ ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በሠማዩ ስፍራ በክብር ላለኸው
ምሥጋናዬ ይኸው ፣ ምሥጋናዬ ይኸው
በሠማዩ ስፍራ በክብር ላለኸው
አምልኮዬ ይኸው ፣ አምልኮዬ ይኸው
አይመረመርም ከፍ ማለቱ የእርሱ ልቀቱ ጌታዬ
አይመረመርም ተወዳዳሪ አቻ ማጣቱ ጌታዬ
አይመረመርም ውበት ቁንጅና ድምቀት ማማሩ ጌታይ
አይመረመርም ግርማ ሞገሱ አስፈሪነቱ ጌታዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሃ ሃ ሃሌሉያ (፬x)
አይመረመርም የርህራሄው የምህረቱ ብዛቱ
አይመረመርም ቸርነቱ ይቅር ማለቱ ጌታዬ
አይመረመርም ፍቅሩ ጥልቀቱ ወርዱ ስፋቱ
አይመረመርም ሰውን መውደዱ አዳኝነቱ ጌታዬ
ሃ ሃ ሃሌሉያ (፬x)
አዝማች · Chorus
ትልቅ ነህ የእኔ አእምሮ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ (፬x)
ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (፫x)
ኦ ትልቅ ነህ አንተ ትልቅ (፫x)
እግዚአብሔር ትልቅ ነው አምላኬ ትልቅ ነው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ትልቅነትህን ያላየ አለ ወይ? (፫x)
ትልቅነትህን ያልሰማ አለ ወይ? (፫x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እኔኮ አይቻለሁ ትልቅነትህን
ከሁኔታ በላይ አንተ መብለጥህን
እኔ አይቻለሁ ትልቅነትህን
ከሁኔታዎች አንተ መብለጥህን
አንተ እኮ እጅግ ትልቅ ነህ (፪x)
አምላኬ እጅግ ትልቅ ነህ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
የዘለዓለም አምላክ የምድር ፈጣሪ
በዘለዓለም ዙፋን ላይ ለዘለዓለም ነዋሪ
የዘለዓለም አምላክ ነፍሴ ታከብርሃለች (፪x)
የነገሥታት ንጉሥ ነፍሴ ታከብርሃለች (፪x)
የዘለዓለም አምላክ ነፍሴ ታከብርሃለች (፪x)
ነፍሴ ታከብርሃለች (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ