Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሥራህ ግሩም እና ድንቅ ነው

Serah Gerum Ena Denq New

2013 · ትራክ 4 · 3:46 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በወጀብ በአውሎ ንፋስ በማዕበል ስንናወጥ

ወጀቡን የሚገስጽ ማዕበሉን የሚያሰኝ ጸጥ

ኢየሱስ

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው (፫x) ጌታ ሆይ

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው (፫x) ጌታ ሆይ

እኛን ያስጨነቀውን ማዕበሉን የሚረግጥ

በውኃ ላይ የሚራመድ እኛንም የሚያራምድ

ኢየሱስ

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው (፫x) ጌታ ሆይ

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው (፫x) ጌታ ሆይ

በእጥፍ የነደደውን እቶኑን የሚያበርድ

በእሳት ውስጥ የሚራመድ እኛንም የሚያራምድ

ኢየሱስ

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው (፫x) ጌታ ሆይ

ሥራህ ግሩምና ድንቅ ነው (፫x) ጌታ ሆይ

ኢየሱስ (፬x)

አምነንህ አላፈርንም ጠብቀን አልከሰርንም

ኢየሱስ የእኛ ጌታ ሁሉንም የረታህ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ