Daniel Amdemichael/Yehonal/Yehonegn Tela
2003 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በምድረ በዳ የሆነኝ ጥላ
ያኔ የተሸከመኝ ሆኖኝ ከለላ (፪x)
ዛሬም ኢየሱስ ከእኔ ጋር ነው
ጊዜና ሁኔታ የማይለውጠው (፪x)
ጌታ ነው ጌታ ዛሬም ጌታ
ጌታ ነው ጌታ ነገም ጌታ (፪x)
አዝማች · Chorus
ነፍሴ በጌታ ሃሴት አደረገች
በጌታ ሃሴት አደረገች
ዛሬም ብድራቱን እያሰበች
ብድራቱን እያሰበች (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በእርሱ ቸርነት አምናን አልፌ
በበረታው ክንድ ላይ ተደግፌ (፪x)
ዛሬ ደስ ብሎኝ እዘምራለሁ
የሠማይን አምላክ አመልከዋለሁ (፪x)
ሃዘኔ ጠፍቶ በደስታ
እዘምራለሁ ለዚህ ጌታ
ሞገስ ለአምላኬ ክብር ይሁን
ልሰዋ ዜማ ያማረውን
አዝማች · Chorus
ነፍሴ በጌታ ሃሴት አደረገች
በጌታ ሃሴት አደረገች
ዛሬም ብድራቱን እያሰበች
ብድራቱን እያሰበች (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ድል አስለምዶኛል ጠላትን ማሸነፍ
ረግጬው አልፋለሁ ሺህ ጦር ቢሰለፍ
ኢየሱስ ነው ጉልበቴ ስልጣንን የሰጠኝ
አሸናፊው ጌታ አሸናፊ ያረገኝ
ዘመን መጣ መጣ የዜማ ወራቱ
ኢየሱስ የሚከብርበት ሲመለክ በቤቱ
ያማረ ዝማሬ ቅኔዉም ለእርሱ ነው
የይሁዳ አንበሳ መታመኛዬ ነው
መታመኛዬ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
መደገፊያ ነው (፪x)
ድል አስለምዶኛል ጠላትን ማሸነፍ
ረግጬው አልፋለሁ ሺህ ጦር ቢሰለፍ
ኢየሱስ ነው ጉልበቴ ስልጣንን የሰጠኝ
አሸናፊው ጌታ አሸናፊ ያረገኝ
ዘመን መጣ መጣ የዜማ ወራቱ
ኢየሱስ የሚከብርበት ሲመለክ በቤቱ
ያማረ ዝማሬ ቅኔዉም ለእርሱ ነው
የይሁዳ አንበሳ መታመኛዬ ነው
መታመኛዬ ነው (፪x)
መደገፊያ ነው (፪x)
መታመኛዬ ነው (፪x)
መደገፊያ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ