እኔማ
Eniema
2003 · ትራክ 13 · 3:44 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እኔማ እንዴት ላውራው
እንዴት ልተርከው ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው
የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
ከእርሱ ጋር ስንጓዝ ባሳለፍኳቸው ዓመታት
ተለይቶኝ አያውቅም ለሰከንድ እንኳን ለሰዓት
ከእስትንፋሴ ይልቅ አምላኬ ለእኔ ቅርቤ ነው
ኢየሱሴ ለእኔ ሁልጊዜ ለእኔ ታማኝ ነው
አዝማች · Chorus
እኔማ እንዴት ላውራው
እንዴት ልተርከው ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው
የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሺህ ቃላቶች አይገልፁትም የጌታዬን ቸርነት
ምህረቱ እጅግ ብዙ ልክ የለው ታማኝነቱ
ጥቂት አልቆጥብም ባለኝ ኃይሌ እዘምራለሁ
ክብር የኢየሱስ ነው ክብርን እሰጠዋለሁ
አዝማች · Chorus
እኔማ እንዴት ላውራው
እንዴት ልተርከው ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው
የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ አምላኬ ይሄ ነው መኩራሪያ የምታመንበት
ኢየሱስ ብዬ ጠርቼው ምንጊዜም የማላፍርበት
ምህረቱን ልዘምር ፍቅሩን ደግሞ ተዓምራቱን
ሞገሱን በላዬ አፍሶታል በረከቱን
አዝማች · Chorus
እኔማ እንዴት ላውራው
እንዴት ልተርከው ኦሆ (፪x)
የአምላኬ ውለታው ከአእምሮ በላይ ነው
የኢየሱስ ስጦታው ከአእምሮ በላይ ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ