ሲነጋ
Sinega
2003 · ትራክ 4 · 4:49 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሲነጋም ሲመሽም
ሁልጊዜ የማስታውሰው
ከልቤ የማይጠፋው
ዘላለማዊው ፍቅርህ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንዴት ይረሳል ያደረግህልኝ?
በቀራንዮ የከፈልክልኝ
ፍቅርህ በሕይወቴ ዛሬም ትኩስ ነው
ግን ቃል አጠረኝ እንዳልተርከው
ብዘምር ቃላቶች ያጥሩኛል
ብናገር ቃላቶች ያጥሩኛል
ለፍቅርህ ምን ምላሽ ይገኛል ኦሆሆ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሲነጋም ሲመሽም
ሁልጊዜ የማስታውሰው
ከልቤ የማይጠፋው
ዘላለማዊው ፍቅርህ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አይታክተኝም ለሃገር ባወራ
ስለ አንተ ክብር ስለ አንተ ዝና
ምነው በሆነ ልቤ እንደ ጅረት
እንደ ውኃ ፈሳሽ እንደ ገነት ምንጭ
አምልኮ ማደሪያህን ይሙላው
ዝማሬ ማደሪያህን ይሙላው
ዕልልታ ማደሪያህን ይሙላው ኦሆሆ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሲነጋም ሲመሽም
ሁልጊዜ የማስታውሰው
ከልቤ የማይጠፋው
ዘላለማዊው ፍቅርህ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ