ይሆናል
Yehonal
2003 · ትራክ 3 · 4:23 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ከጥንት ጀምሮ እንደተናገረኝ (፪x)
የተስፋ ቃሉን ፈፅሞ ይኸው አስደነቀኝ
ዛሬስ አስደነቀኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ይገርማል ይደንቀኛል የእርሱ ሥራ
የትኛው የቱን ትቼ የቱን ላውራ (፪x)
በቀንም በምሽትም በሌሊቱ
ምሥጋና ይድረሰው በየዕለቱ (፪x)
አዝማች · Chorus
አምላኬ ከጥንት ጀምሮ እንደተናገረኝ (፪x)
የተስፋ ቃሉን ፈፅሞ ይኸው አስደነቀኝ
ዛሬስ አስደነቀኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያለውን የሚፈፅም የማይረሳ
በቃሉ ታማኝ ነው የእኔ ጌታ (፪x)
በጊዜው ከተፍ የሚል የሚደርስ
እኔም ዛሬ ቆሜ ሥሙን ልወድስ (፪x)
ይሆናል እርሱ/ጌታ ያለው ይሆናል
ሰው በከንቱ ኧረ ለምን ይጨነቃል
እግዚአብሔር ያለው ይሆናል (፪x)
አዝማች · Chorus
አምላኬ ከጥንት ጀምሮ እንደተናገረኝ (፪x)
የተስፋ ቃሉን ፈፅሞ ይኸው አስደነቀኝ
ዛሬስ አስደነቀኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ