በገናውን
Begenawen
2003 · ትራክ 6 · 5:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በገናውን እጄ እየደረደረ
አፌም ምህረትህን እየተናገረ
መንፈሴና ነፍሴ በአንድነት:ተስማምተው
ያመሰግኑሃል ጌታ ክበር ብለው ኦሆሆ
በምሥጋና የተፈራህ በአምልኮ ኦሆሆ
አምላኬ ሆይ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ (፪x)
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተመስገን ሳልል መሰውያው ሳይከፈት
አፌ ሳይጠራህ ፀሐይ አትጠልቅም
ልኡል ነህ መልካም ሥምህ ያማረ
ዙፋንህ ከጥንት የተከበረ
አዝማች · Chorus
በገናውን እጄ እየደረደረ
አፌም ምህረትህን እየተናገረ
መንፈሴና ነፍሴ በአንድነት:ተስማምተው
ያመሰግኑሃል ጌታ ክበር ብለው ኦሆሆ
በምሥጋና የተፈራህ በአምልኮ ኦሆሆ
አምላኬ ሆይ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ (፪x)
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
ቁጥር 2 · Verse 2
የገባኝ ነገር የተረዳሁት
ልቤ ውስጥ አለ ከአንተ ያገኘሁት
ዝም በል ቢሉኝ አይሆንልኝም
የገባኝ ፍቅርህ አያስችለኝም
አዝማች · Chorus
በገናውን እጄ እየደረደረ
አፌም ምህረትህን እየተናገረ
መንፈሴና ነፍሴ በአንድነት:ተስማምተው
ያመሰግኑሃል ጌታ ክበር ብለው ኦሆሆ
በምሥጋና የተፈራህ በአምልኮ ኦሆሆ
አምላኬ ሆይ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ (፪x)
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
ቁጥር 3 · Verse 3
ያማረ ዜማ ነፍሴ አፈለቀች
ለአንተ ክብር ይሁን እያለች
እደሰታለሁ አምላኬ አንተ ነህ
ታማኙ ጌታ እንከን የሌለህ
አዝማች · Chorus
በገናውን እጄ እየደረደረ
አፌም ምህረትህን እየተናገረ
መንፈሴና ነፍሴ በአንድነት:ተስማምተው
ያመሰግኑሃል ጌታ ክበር ብለው ኦሆሆ
በምሥጋና የተፈራህ በአምልኮ ኦሆሆ
አምላኬ ሆይ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ (፪x)
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
የለም እኮ ኧረ እንዳንተ የለም እኮ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ