ድንቅ ነህ
Denq Neh
2005 · 5:31 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያለፈውን ዘመን ታሪክ አገላብጠን
ሕይወትን ግራና ቀኙን ተመልክተን
አንድ እውነት ተረዳን ጠንቅቀን አውቀናል
እግዚአብሔር ብቻ ነው አምላክ ነህ ብለናል
ለተቸገረው ሰው ፈጥነህ የምትደርስ
ሲጠሩህ የምትሰማ በእሳት የምትመልስ
የኤልያስ አምላክ ዛሬስ መች ደክመሃል
በስምህ ተወራርደን ስንቱን ድል አድርገናል
አዝማች · Chorus
ለአምላክነትህ በነፍስ ተወራርደን
ሁሉንም ጣልንና አንተን ተከተልን (፪x)
በዘመናት መሃል በድል ተሻግረናል
ልንክደው አንችልም ክንድህን አይተናል
ድንቅ ነህ ታደንቀናለህ (፬x)
ግሩም ነህ ታስገርመናለህ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በችርነትህ አመታትን ለህዝብህ ታቀናጃለህ
ምድረ በዳው ስብ ይጠግባል ባሕሩን ታሻግራለህ
ከጠላት ዛቻ በሚገርም ታምራትህ ካመለጥን
በነፍሳችን ተወራርደን ይገባል አንተን ልናምን
ቁጥር 3 · Verse 3
ይውጣ እንጂ ያየታሪክ መዝገብ
ቁጥር 4 · Verse 4
ያደረከው በይፋ ይነበብ
እውነት ነው ዘመን ይናገራል
እግዚአብሔር ኧረ እንዳንተ የታል (፪x)
ድንቅ ነህ ታደንቀናለህ (፬x)
ግሩም ነህ ታስገርመናለህ (፬x)
ሁሉን ወደ ኋላ ጥለን ተከተልንህ
እንደወደድክ አርገህ ይሄው ምራን አልንህ
ምች ከሰርን ታዲያ በብዙ አትርፈናል
በአንተ እንዳማረብን ጉዑዙ ይናገራል
በሚታየው ነገር ሕይወትን ሳንተምን
በእምነት ከቃልህ ጋር መራመድ መረጥን
ከዚህ ዓለም ክፋት ስምህ አድኖናል
ስትደግፈን ያዩ ድንቅ ነህ ብለዋል
አዝማች · Chorus
ለአምላክነትህ በነፍስ ተወራርደን
ሁሉንም ጣልንና አንተን ተከተልን (፪x)
በዘመናት መሃል በድል ተሻግረናል
ልንክደው አንችልም ክንድህን አይተናል
ድንቅ ነህ ታደንቀናለህ (፬x)
ግሩም ነህ ታስገርመናለህ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ