የበላይ
Yebelay
2005 · ትራክ 1 · 5:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከአንተ ጋር የሚቆም ደፍሮ የሚወዳደር
(የበላይ አሃሃ የበላይ)
አልተገኘም በምድር ከጫፍ ጫፍ ቢቆጠር
(የበላይ አሃሃ የበላይ)
ሥምህ ብቻ አይደለም ሥምህ ይናገራል
(የበላይ አሃሃ የበላይ)
የትኛው ጀግና ሰው መቃብር ፈንቅሏል
(የበላይ አሃሃ የበላይ) (፪x)
አዝማች · Chorus
የበላይ ነህ ጌታ የበላይ የሁሉ በላይ
በላይ (፫x) የበላይ የሁሉ በላይ (፪x)
የበላይ የሁሉ በላይ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ ሃያላንን በምድር ላይ አይተናል
ማኅደር ሲገለጥ ታሪክ አንብበናል
የትኛው ጀግና ነው ሞትን ያሸነፈው
ስንቱን ወንድ አይደል ወይ መቃብር የዋጠው
አንተ ግን ከፍ ብለሃል
ሞትና መውጊያውን ሰብረሃል
ልኩራ እንጂ በአንተ እንዴት ልፈር
ጌታ ነህ ታሪክ ይናገር (፪x)
አዝማች · Chorus
የበላይ ነህ ጌታ የበላይ የሁሉ በላይ
በላይ (፫x) የበላይ የሁሉ በላይ (፪x)
የበላይ የሁሉ በላይ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስቲ ይናገሩ ሰማይና ምድር
(የበላይ አሃሃ የበላይ)
የታሪክ አዋቂ ይጠራ/አምጡልኝ ምስክር
(የበላይ አሃሃ የበላይ)
ከአንተ/ከእኔ ጌታ በላይ : ሞትን ድል ያደረገ
(የበላይ አሃሃ የበላይ)
እረ ማነው እርሱ በክብር ያረገ
(የበላይ አሃሃ የበላይ) (፪x)
አዝማች · Chorus
የበላይ ነህ ጌታ የበላይ የሁሉ በላይ
በላይ (፫x) የበላይ የሁሉ በላይ (፪x)
የበላይ የሁሉ በላይ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ