ኢየሱስ
Eyesus
2005 · ትራክ 4 · 4:56 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀኑ እንዴት ይገፋል ያለመጨነቅ
በሃሳብ ማጥ ውስጥ መማቀቅ (፪x)
ሳይሞላለት ዛሬን ነገን ሲፍጨረጨር
በሥጋት ብዛት ሲወጠር (፪x)
የሰው ሕይወት በምድር ሰልፉ እንዴት ብርቱ ነው
ማነው ከዚህ መዓት የሚገላግለው
አዝማች · Chorus
የሁሉ ቁልፍ በእጁ ያለው
መፍትሄው ኢየሱስ ብቻ ነው (፪x)
ኢየሱስ (፲፪x)
የሁሉን ሚስጥር ቁልፉን ይዘሃል
በአሰራርህ ማን ይመስልሃል
በሰማይ በምድር ስልጣን የአንተ ነው
እንዲህ አታድርግ የሚልህ ማነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ሕይወትም በድንገት ሲለብስ ደመና
ደጅ ሲወጣ ገበና (፪x)
ያላሰቡት ሲደርስ ያሰቡት ሳይሞላ
ሰው ከእርሱ ጋር ሲጣላ (፪x)
የሰው ሕይወት በምድር ሰልፉ እንዴት ብርቱ ነው
ማነው ከዚህ መዓት የሚገላግለው
አዝማች · Chorus
የሁሉ ቁልፍ በእጁ ያለው
መፍትሄው ኢየሱስ ብቻ ነው (፪x)
ኢየሱስ (፲፪x)
የሁሉን ሚስጥር ቁልፉን ይዘሃል
በአሰራርህ ማን ይመስልሃል
በሰማይ በምድር ስልጣን የአንተ ነው
እንዲህ አታድርግ የሚልህ ማነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ