የሚያኮራ ጌታ
Yemiyakora Gieta
2005 · ትራክ 11 · 5:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"ከቶ አይቸኩልም ዘግይቶ ይነሳል
ግን ማንም አይቀድመው ፈጥኖ ይደርሳል
በምድረ በዳ ምንጭ የሚያፈልቀው
ይሄ ነው እግዚአብሔር የምናመልከው
አንተ የምትተኛ ንቃ ተነሳ
ክርስቶስ ከላይ ያበራልሃል
ሃይል ለሌለው ሃይል ይጨምራል
የደከመው መደገፍያ"
አዝማች · Chorus
ለደከመው ህይልን ያስታጥቃል
የሞተውን በሕይወት ያኖራል
ለስልጣኑ ማነው ያልተረታ
ዛሬም ነገም የሚያኮራ ጌታ (፪x)
የሚያኮራ ጌታ የሚያኮራ (፬x)
የሚያስመካ ጌታ የሚያስመካ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በእሳቱ ውስጥ አለፍኩ አላቃጠለኝም
በወንዙ ላይ ቆሜ አላሰጠመኝም
ምህረቱ እንደጋሻ ሆኖ እየከለለኝ
ጠላቴ ሞቷል ሲል በሕይወት አለሁኝ
አዲሱን ዝማሬ ይዤ ወጥችሃለሁ
የጠላቴን መንደር አሸብረዋለሁ
አምላኬ እንደንስር ሃይሌን አድሶታል
ስሙን እየጠራሁ ቀንበር ይሰበራል
አዝማች · Chorus
ለደከመው ህይልን ያስታጥቃል
የሞተውን በሕይወት ያኖራል
ለስልጣኑ ማነው ያልተረታ
ዛሬም ነገም የሚያኮራ ጌታ (፪x)
የሚያኮራ ጌታ የሚያኮራ (፬x)
የሚያስመካ ጌታ የሚያስመካ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቀይ ባሕር ከፊቴ ቆሞ ሲያስጨንቀኝ
ሰራዊት እሁአላ ተግቶ ሲከተለኝ
እጆቼን አንስቼ አምላኬን ጠራሁኝ
ሰመጠ ፈርዖን በዐይኖቼ እያየሁኝ
በተዐምር ነው እኮ ጌታ የሚያኖረኝ
ስንትን አሳልፎ ቅጥሩን አዘለለኝ
ባሕር ተከፍሎልኝ በድል ተሻግሬ
አልጠገብኩም ገና ለክብሩ ዘምሬ
አዝማች · Chorus
ለደከመው ህይልን ያስታጥቃል
የሞተውን በሕይወት ያኖራል
ለስልጣኑ ማነው ያልተረታ
ዛሬም ነገም የሚያኮራ ጌታ (፪x)
የሚያኮራ ጌታ የሚያኮራ (፬x)
የሚያስመካ ጌታ የሚያስመካ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ