Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምንሃለሁ ጌታ

Amnehalehu Gieta

2005 · ትራክ 9 · 5:25 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አምንሃለሁ ጌታ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ኢየሱስ አምንሃለሁ (፪x)

ጭር ባለው ደረቅ ምድረ በዳ ውኃ አፍልቀህልኝ ጠጥቻለሁ (፪x)

አምንሃለሁ ጌታ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ኢየሱስ አምንሃለሁ (፪x)

ጭር ባለው ደረቅ ምድረ በዳ ውኃ አፍልቀህልኝ ጠጥቻለሁ (፪x)

ጨለማው እጅግ በርትቶ

ተስፋ የሚጣልበት ጠፍቶ

ግራ ቀኝ በሩ ሲዘጋ

ተጣራሁ ረዳት ፍለጋ

ጩኸቴን ሰምተህ ከሰማይ

ወርደሃል በጠላቴ ላይ

ወጀቡን ጸጥ አረክልኝ

ኢየሱስ ጋሻ ሆንክልኝ (፪x)

አምንሃለሁ ጌታ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ኢየሱስ አምንሃለሁ (፪x)

ጭር ባለው ደረቅ ምድረ በዳ ውኃ አፍልቀህልኝ ጠጥቻለሁ (፪x)

ኢየሱስ የነፍሴ መድሃኒት

ኢየሱስ ድንቅ የሰራኅልኝ

ኢየሱስ ተራራውን ንደህ

ኢየሱስ ሜዳ አደረክልኝ

ኧረ አይቻልም ከእንግዲህስ አልልም

በዐይኔ አይቻለሁ አልጠራጠርም

አንተ ይሁን ካልክ የማይሆን ይሆናል

ወደደም ጠላም ፍጥረት ይሰማሃል

ጌታ ነህ (፪x) ማን ይቃወምሃል

ባሕሩን ስትከፍለው ዐይኖች አይተውሃል

ጌታ ነህ (፪x) ኢየሱስ ማን ይቃወምሃል

ባሕሩን ስትከፍለው ዐይኖች አይተውሃል

አምንሃለሁ ጌታ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ኢየሱስ አምንሃለሁ (፪x)

ጭር ባለው ደረቅ ምድረ በዳ ውኃ አፍልቀህልኝ ጠጥቻለሁ (፪x)

አምንሃለሁ ጌታ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ኢየሱስ አምንሃለሁ (፪x)

ጭር ባለው ደረቅ ምድረ በዳ ውኃ አፍልቀህልኝ ጠጥቻለሁ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ