ኢትዮጵያ
Ethiopia
2005 · ትራክ 8 · 6:16 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ ሀገሬ እጆችሽን የምትዘረጊበት
ሰዓቱ ደርሷል እንባ ሚደርቅበት ካፈርሽ
ሰላም ይታጨዳል ከወንዝሽ
ዓለም ይባረካል ዓለም ይባረካል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አያለሁ አዲስ ቀን ከደመናው ማዶ
ብርሃን ሲወጣልሽ ጨለማውን ቀዶ
የራቁት ልጆችሽ ይሰበሰባሉ
እውነትም እግዚአብሔር ሃያል ነው እያሉ
ባማሩት መቅደሶች ወንጌል ይሰበካል
ህጻን ሽማግሌው ለአምላክ ክብር ያመጣል
እግዚአብሔርም ቃሉን በታምር ያጸናል
ሊሰራ ሲወጣ ማን ይቃወመዋል ማን የከለክላል
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ ሀገሬ እጆችሽን የምትዘረጊበት
ሰዓቱ ደርሷል እንባ ሚደርቅበት ካፈርሽ
ሰላም ይታጨዳል ከወንዝሽ
ዓለም ይባረካል ዓለም ይባረካል
ቁጥር 2 · Verse 2
እውቀትና ጥበብ ከአምላክ የተዋሉ
ኃጢያትን ጠልተው ለጽድቅ የሚኖሩ
ልዋይና ዝና ከቶ ማይገዛቸው
ለፍርድና ለእውነት ቅናት የበላቸው
ልጆች አሉሽ ገና ተግተው የሚነሱ
ለምስኪኑ መውደቅ ከልብ የሚሳሱ
የተገባልሽ ቃል በእርግጥ ይፈጸማል
አምላክሽ ሊያድንሽ ሊታደግሽ ወጥቷል ሊታደግሽ ወጥቷል
አዝማች · Chorus
ኢትዮጵያ ሀገሬ እጆችሽን የምትዘረጊበት
ሰዓቱ ደርሷል እንባ ሚደርቅበት ካፈርሽ
ሰላም ይታጨዳል ከወንዝሽ
ዓለም ይባረካል ዓለም ይባረካል (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ