Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ኃያል

Egziabhier Hayal

ትራክ 11 · 3:55 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ኃያል

በሰልፉም ደግሞ ኃያል

ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (፪

ህዝቡን ከልሎ የሚዋጋ

ለጠላት ዛቻ የማይሰጋ

ብድራትን መላሽ የእኛ አምላክ

ይርታ እንጂ መረታትን አያውቅ (፪x)

እግዚአብሔር ኃያል

በሰልፉም ደግሞ ኃያል

ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (፪x)

የእምነት ባለድል ሳይጸጸት

ጌታን አምኖ ሰው አያፍርበት

ለተስፋው ፈቶ ሰንሰለት

ሕይወቱን ሰጥቷል ሳትሰስት (፪x)

እግዚአብሔር ኃያል

በሰልፉም ደግሞ ኃያል

ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (፪x)

አንተም በኃይሉ ድል ነስተህ

በእቶን ተፈትነህ ነጥረህ

ለመንግሥቱ ብቁ ሆነህ

እንድትወጣ ጌታ ይርዳህ (፪x)

እግዚአብሔር ኃያል

በሰልፉም ደግሞ ኃያል

ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (፪x)

ያን ጊዜ ተዋግቶ የረታ

የጠላቱን ጅማት የፈታ

በፅኑ አመታት የሚመታ

ሁሉን የሚችል የድል ጌታ (፪x)

እግዚአብሔር ኃያል

በሰልፉም ደግሞ ኃያል

ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ