Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ልጅነቴ ያላለቀ

Lejenetie Yalaleqe

ትራክ 7 · 2:35 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ልጅነቴ ያላለቀ ነኝና ብላቴና

ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (፪x)

በግብዝነት ተሯሩጬም ከእውነትህም ተሳሰቼ

በስሜት ተገፋፍቼ የቃልህን ሙላት አጥቼ

እንዳልጠፋ በጠላት ተጠቅቼ

ልጅነቴ ያላለቀ ነኝና ብላቴና

ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (፪x)

ለጋነቴ እኔን አጋልጦኝ መከራውም አጠውልጐኝ

አውሎ ነፋስ አፍገምግሞኝ የአሸዋው መሠረት አዝሞኝ

ክፉኛ ገፍትሮ እንዳይጥለኝ

ልጅነቴ ያላለቀ ነኝና ብላቴና

ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (፪x)

ወተት ብቻ መጋቱን ትቼ አጥንቱንም ደግሞ በልቼ

እንደ ህጻን ማሰቤ ቀርቶ በጐልማሳነት ተተክቶ

ላይ እሻለሁ ሕይወቴ ተገንብቶ

ልጅነቴ ያላለቀ ነኝና ብላቴና

ሙሉ ሰው አድርገኝ ጌታ ቃልህን አብላኝና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ