የማይናወጥ መሰረቴ
Yemayenawet Meseretie
ትራክ 12 · 4:19 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የማይናወጥ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ መከታዬ
የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዚያ ሸለቆ በሀዘኑ ቦታ
ኢየሱስ አልተውከኝም ደጋፊ እንዳላጣ
ሕይወቴ ነህና ተድላ መከታዬ
ኢየሱስ ከአንተ በቀር የቱ ነው ጋሻዬ
አዝማች · Chorus
የማይናወጥ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ መከታዬ
የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ
ቁጥር 2 · Verse 2
የዓለሙ ወጀብ ሊመታኝ ሲቃጣ
ጌታ አለቀቀኝም ከእጁ እንድወጣ
ወደ እርሱ የመጡትን ልጆቹን ያፈቅራል
በእቅፉ ውስጥ ይዞ ይጠብቃቸዋል
አዝማች · Chorus
የማይናወጥ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ መከታዬ
የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ
ቁጥር 3 · Verse 3
የጣርህን መጠን በምን ልገምተው
የውለታህን ልክ በምን ላስተውለው
ከቶ እንዳልዘነጋው ያንን መስቀልህን
ደግሞም እንዳልረሳ ለእኔ ማንባትህን
አዝማች · Chorus
የማይናወጥ መሠረቴ
ጌታ ኢየሱስ መከታዬ
የህመሜ ፈውስ መድኃኒቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ