እምቢ
Embi
ትራክ 14 · 4:06 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሙታን ባልንጀራ ኃጢአተኛ ሳለሁ
ጌታን በማመኔ ከክፋት ድኛለሁ
ግን ሕይወቴን እንድክድ አሁን ብከተልም
ኢየሱሴን ክጄ ግኡዝ አላመልክም
አዝማች · Chorus
እምቢ አሻፈረኝ ለምስሉ አልሰግድም
ለሰው እጅ ሥራ አልንበረከክም
ከናቡከደናጾር የቁጣ ነበልባል
የማመልከው ጌታዬ በእርግጥ ያድነኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
እቶኑ ይታየኛል ግለቱ ይሰማኛል
ፈርቼ አልጠላውም አንስቶ ያጠራኛል
ለሰማያዊው መንግሥት ብቁ ያደርገኛል
ሰው እንደሚያስበው መቼ ይጐዳኛል
አዝማች · Chorus
እምቢ አሻፈረኝ ለምስሉ አልሰግድም
ለሰው እጅ ሥራ አልንበረከክም
ከናቡከደናጾር የቁጣ ነበልባል
የማመልከው ጌታዬ በእርግጥ ያድነኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
በእሳት ውስጥ ያሉትን ጭሱ ሳይነካቸው
አስረው የጣሏቸው ወላፈን ፈጃቸው
እንደዚህ የሚሰራ ኃያል ጌታ ካለኝ
ሰባት እጥፍ ያንድድ እኔ ምን ቸገረኝ
አዝማች · Chorus
እምቢ አሻፈረኝ ለምስሉ አልሰግድም
ለሰው እጅ ሥራ አልንበረከክም
ከናቡከደናጾር የቁጣ ነበልባል
የማመልከው ጌታዬ በእርግጥ ያድነኛል
ቁጥር 4 · Verse 4
እምቢ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ