Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ፍቅር ነህ

Feqer Neh

6:53 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የዘላለም አምላክ የትውልድ መጠጊያ

የፍጥረት መጋቢ ድጋፍ መሸሸጊያ

ልጅህን በመስጠት ፍቅርን የተገበርክ

ዓለሙን በሙሉ እንዲሁ የወደድክ

ፍቅር ነህ እግዚአብሔር

ይቅር ባይ የምትምር

እልፍ ነው ቸርነትህ

አይቆጠር (አይነገር ) ማጽናናትህ(፪x)

ፍቅር ነህ ፍቅር ነህ እያልኩ ባዜምልህ

ደግሞ በአዲስ ምሕረት ታስደንቀኛለህ

አምላኬ አምላኬ እልሃለው እጠራሃለው ደግሜ

ልዩ ነው አወዳደድህ ላዚምልህ ፊትህ ቆሜ

ምን ዓይነት ፍቅር ነህ

እንዴት ያለህ መሃሪ(ወዳጅ) ነህ (፪x)

የዘላለም አምላክ የትውልድ መጠጊያ

የፍጥረት መጋቢ ድጋፍ መሸሸጊያ

ልጅህን በመስጠት ፍቅርን የተገበርክ

ዓለሙን በሙሉ እንዲሁ የወደድክ

ፍቅር ነህ እግዚአብሔር

ይቅር ባይ የምትምር

እልፍ ነው ቸርነትህ

አይቆጠር (አይነገር ) ማጽናናትህ(፪x)

የሕይወት ምንጭ ነህ ፍቅርን ለተጠማ

የምታለመልም ነፍስን የምታረካ

አውርቼ አውርቼ አልጠግብም አይገልጽህም ቃላቴ

ደግነትህን ብዘምር አልገልጸውም በዚህ አንደበቴ

ምን ዓይነት ፍቅር ነህ

እንዴት ያለህ መሃሪ(ወዳጅ) ነህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ